፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 07 2016| NBC ETHIOPIA-በእርስ በርስ ጦርነት እየተጎዳች የምትገኘው ሱዳን በመጪው መስከረም 7መቶ 56 ሺህ የሚሆኑት ዜጎቿ ለከፋ ረሀብ ሊጋለጡ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡፡
ከአንድ ዓመት በላይ የተሻገረው የሱዳን ጦርነት ከሞት፤ ስደተና መፈናቀል ባሻገር የረሀብ አደጋ ማንዣበቡ ሁኔታውን አስከፊ ሊያደርገው ይችላል እየተባለ ነው ፡፡
ጥናቶች እንዲሚያሳዩት 18 ሚሊዮን የሱዳን ህዝብ ወይም ከሶስቱ አንዱ ከፍተኛ ደረጃ የምግብ እና ደህንነት ስጋት ሲኖርበት፤ አምስት ሚሊዮን የሚሆነው ደግሞ አፋጣኝ መፍትሄ የሚሻ የረሀብ አደጋ ተጋርጦበታል፡፡
በሱዳን ጦርነት ምክንያት የተከሰተው ረሀብ 8 ነጥብ 2 ሚሊዮን ህዝብ እንዳፈናቀለ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡ ዘገባው የሮይተርስ ነው ፡፡
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












