Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Uncategorized

የዓለማችን ታዋቂ እና ውድ ስዕሎች

June 14, 2024
in Uncategorized
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ሰኔ 07 2016| NBC ETHIOPIA-ጅማሮውን በዋሻ ላይ ያደረገው የስዕል ጥበብ በዘመናት ተቃኝቶ እየረቀቀ እና ይበልጡን እየተወደደ መዝለቅ የቻለ የጥበብ ውጤት ነው፡፡  ቴክኖሎጂ  መልክ እና ቀለሙን ሳይለውጠው እና ሳያደበዝዘው በዘመን ተሸጋሪነት ዛሬም ታሪክን፣ ባህልን፣ የፈጠራ ውጤትን በቀለማት አዋህዶ እየተናገረ ይገኛል፡፡

ለዛሬም የጎላ የጥበብ አሻራ ያረፈባቸው እንዲሁም ዘመናትን ተሻገረው መዝለቅ ከቻሉ የዓለማችን ዝነኛ እና እጅን በአፍ የሚስጭኑ ከተባለላቸው ስዕላት መካከል  የተወሰኑት ልናስቃኛችሁ ወደድን።

በቅድሚያ የምናገኘው በአያሌ ሙያዎቹ በሚታወሰው ጣሊያናዊው አርቲስት በሊዮናርዶ ዳቪንቺ የተሳለውን የሞናሊዛ ስዕልን ነው።ይህንን ስዕል ከህጻን እስከ አዋቂ አይቶት ወይም ስለስዕሉ ሲወራ ሰምቶት ማያውቅ የለም ቢባል ጥቂቱ ነው፡፡

ሊዮናርዶ ዳቪንቺ በቅንድብ አልባነት በምትታወቀው፣ በመሳቅና በመኮሳተር መሀል ሆና በተሳለችው ሥዕሉ ሞናኒዛ እጅጉኑ ይታወቃል።

በጎርጎርሳውያኑ ከ1503 እስከ 1519 ድረስ እንደተሳለ የሚነገርለት  የሞናሊዛ ስዕል በዓለም ላይ በጣም ውዱ ሥዕል ብቻ ሳይሆን በብዛት የተጎበኘ፣ በርካታ ውይይቶች የተደረጉበት፣ ብዙዎች የፃፉለት፣ በበርካታ ቋንቋ የተሞዘቀለት እና የተመሰገነ የዓለማችን ድንቅ የስዕል ጥበብ  ነው።  

ስዕሉ በ77 ሳ.ሜ የቁመት መጠንና በ53ሳ.ሜ የአግድሞሽ ቁመት በተወጠረ ሸራ ላይ የተሳለ ሲሆን፣ ከዓለማችን ውድ ስዕሎች መካከልም አንዱ ነው። በ1962 ለዚሁ ስዕል የ100 ሚሊየን ዶላር ኢንሹራንስ ተገብቶለታል። እ.ኤ.አ በ2018 ዋጋው ወደ 650 ሚሊየን ዶላር አድጓል። ይሄም በጊነስ ወርልድ ሪከርድ ላይ ቀዳሚ ሆኖ እንዲሰፍር አድርጎታል።

የሞናሊዛ ስዕል ከፈረንሳይ ሪፐብሊክ እጅግ ውድ ከሆኑ ንብረቶች መካከል አንዱ ነው። በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ በጣም ታዋቂ ከሆኑት ሙዚየሞች አንዱ በሆነው በፓሪስ ሉቭር ውስጥ በክብር ተቀምጦ ይገኛል።


በቀጣይ የምናገኘው የአለማችን እጅግ ታዋቂው እና ወዱ ስዕል ኢየሱስ ከመሰቀሉ በፊት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የተካፈለውን የመጨረሻውን እራት መነሻ ተደርጎ የተሳለው ትልቅ የግድግዳ ሥዕል ነው።

በጎርጎርሳውያኑ ከ1503 እስከ 1519 ድረስ እንደተሳለ የሚነገርለት  የሞናሊዛ ስዕል በዓለም ላይ በጣም ውዱ ሥዕል ብቻ ሳይሆን በብዛት የተጎበኘ፣ በርካታ ውይይቶች የተደረጉበት፣ ብዙዎች የፃፉለት፣ በበርካታ ቋንቋ የተሞዘቀለት እና የተመሰገነ የዓለማችን ድንቅ የስዕል ጥበብ  ነው።  

ስዕሉ በ77 ሳ.ሜ የቁመት መጠንና በ53ሳ.ሜ የአግድሞሽ ቁመት በተወጠረ ሸራ ላይ የተሳለ ሲሆን፣ ከዓለማችን ውድ ስዕሎች መካከልም አንዱ ነው። በ1962 ለዚሁ ስዕል የ100 ሚሊየን ዶላር ኢንሹራንስ ተገብቶለታል። እ.ኤ.አ በ2018 ዋጋው ወደ 650 ሚሊየን ዶላር አድጓል። ይሄም በጊነስ ወርልድ ሪከርድ ላይ ቀዳሚ ሆኖ እንዲሰፍር አድርጎታል።

የሞናሊዛ ስዕል ከፈረንሳይ ሪፐብሊክ እጅግ ውድ ከሆኑ ንብረቶች መካከል አንዱ ነው። በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ በጣም ታዋቂ ከሆኑት ሙዚየሞች አንዱ በሆነው በፓሪስ ሉቭር ውስጥ በክብር ተቀምጦ ይገኛል።


በቀጣይ የምናገኘው የአለማችን እጅግ ታዋቂው እና ወዱ ስዕል ኢየሱስ ከመሰቀሉ በፊት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የተካፈለውን የመጨረሻውን እራት መነሻ ተደርጎ የተሳለው ትልቅ የግድግዳ ሥዕል ነው።

ስእሉ ከሊዮናርዶ ዳቪንቺ ዝነኛ እና ታዋቂ ስራዎች መካከል ከሞናንዛ በመቀጠል  የምናገኘው  የስዕል ጥበብ የፈሰሰበት ነው።

በጎርጎሮሳውያኑ ከ1495 እስከ 1498 ጣሊያን በሚገኘው የሳንታ ማሪያ ዴሌ ግራዚ ገዳም እንደተሳለ ይነገርለታል። በ460ሳ.ሜ የቁመት መጠንና በ880ሳ.ሜ የአግድሞሽ ቁመት የሚለካ ሲሆን፣ በገዳሙ የሚገኘውን የመመገቢያ አዳራሽ አጠቃላይ ግድግዳን ይሸፍናል።

ሥዕሉ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ አሳልፎት እንደሚሰጥ የተናገረበትን እና 12ቱ ደቀ መዛሙርት በተለያዩ ስሜቶች እና ገጽታዎች ያስመለክተናል።

ይህ ስዕል በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በአንዳንድ ጥቃቶች፣ በእርጥበት እንዲሁም በተወሰነ መልኩ ጉዳት ቢደርስበትም  ዛሬም ድረስ ከዳ ቪንቺ በጣም የተከበሩ እና የተጠኑ ስራዎች አንዱ ሆኖ ዘመናት መሻገር የቻለ ሆንዋል።

የሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ የመጨረሻው እራት ሥዕል በአሁኑ ጊዜ በሚላን ፣ ጣሊያን በሚገኘው የሳንታ ማሪያ ዴል ግራዚ ገዳም ሪፌቶሪ (የመመገቢያ አዳራሽ) ውስጥ ይገኛል።

በሆላንዳዊው አርቲስት ቪንሰንት ቫን ጎግ የተሳለው ‹‹ስታርሪ ናይት›› ሥዕል ሌላኛው የዓለማችን እውቁ የስዕል ጥበብ ስራ ነው።

ስታርሪ ናይት በጎርጎሮሳውያኑ በ1889 የተሳለ በፈረንሳይ ሴንት-ሬሚ በሚገኘውን ቅዱስ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ከውስጥ ሆኖ በመስኮት በኩል ወደውጪ ያለውን እይታ የሚያስመለክት ስዕል ነው።

በሥዕሉ ላይ ተለዋዋጭ የሌሊት ሰማይ እና ጨረቃ ያሳያል። ስታርሪ ናይት ሥዕል ከቫን ጎግ  ዝነኛ እና የተከበሩ ሥዕሎች አንዱ ነው።

ይህ ስዕል በ73 ሴሜ ሳ.ሜ የቁመት መጠንና በ92 ሴ.ሜ) ሳ.ሜ የአግድሞሽ ቁመት በሸራ ላይ ያረፈ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ ከ1941 ጀምሮ ለእይታ በቀረበበት በኒውዮርክ  የዘመናዊ ጥበብ ሙዚየም (ሞኤምኤ) ዛሬም ለጎብኚዎች ክፍት እንደሆነ ነው።

እ.ኤ.አ. በ2017 አምስተርዳም የሚገኘው የቫን ጎግ ሙዚየም የስዕሉ ዋጋ ከ100 ሚሊየን ዶላር በላይ ኢንሹራንስ ገብቶለታል።

ስታርሪ ናይት ቫን ጎግ ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ጥልቅ ግንኙነት እና የተፈጥሮን አለም በጥልቅ ግላዊ እና መንፈሳዊ ፍቺው በኪነጥበብ የመሙላት ችሎታውን ያሳየበት ስዕሉ መሆኑን ይነገራል።

በዓለም ላይ ካሉት እጅግ ታዋቂ የጥበብ ስራዎች አንዱ ነው።The Scream ይህ የዓለማችን ታዋቂ ስዕል በጎርጎሮሲያኑ በ1893 በኖርዌያዊው አርቲስት ኤድቫርድ ሙንች ተስሏል።

The Scream ቀይ ብርቱካንማ ሰማይ ላይ እጆቹን ጭንቅላቱ ላይ አደርጎ ከባድ ጩኸት የሚያሰማን ሰውን ያስመለክታል።

በዓለም ላይ ካሉ በጣም ውድ ሥዕሎች አንዱ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ 2012 በ 120 ሚሊዮን ዶላር በጨረታ ተሸጧዋል፡፡ ይህም በወቅቱ ከተሸጡ የጥበብ ስራዎች እጅግ ውዱ ነበር፡፡

ይህ የዓለማችን ታዋቂ ስዕል  ከ1893  በኦስሎ, ኖርዌይ በሚገኘው ብሔራዊ ሙዚየም ውስጥ ተቀምጦ ይገኛል።

 “ጉርኒካ” በስፔናዊው አርቲስት ፓብሎ ፒካሶ የተሳለ ሌላኛው የዓለማችን ታዋቂውን ዝነኛው የስዕል ጥበብ ነው።

በጎርጎሮሳውያኑ በ1937 በስፔን የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት በጊርኒካ ከተማ ለደረሰው የቦምብ ጥቃት በ‹‹ፒካሶ››  ጥበብ  ምላሽ የተሰጠበት ስለመሆኑ ይነገራል።

በስፔን የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት በባስክ ክልል በጊርኒካ ከተማ ጀርመን የወሰደችውን የአየር ላይ የቦምብ ጥቃትን በመታሰቢያነት ያሰፈረው ሥዕሉ፣ ከ11 ጫማ በላይ ቁመት እና ከ25 ጫማ ስፋት አለው፡፡ በእያንዳንዱ የስዕሉ ቀለማት የጦርነትን አስፈሪነት ፍንትው አድርጎ አሳይቷል፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ለዕይታ የቀረበው እ.ኤ.አ በ1937 በስፔን ፓቪልዮን ሲሆን፣ ከዚያም በ1981 ማድሪድ በሚገኘው ሬና ሶፊያ ሙዚየም ውስጥ ከመቀመጡ በፊት ለ20 ዓመታት ያህል በዓለም ዙሪያ ተዘዋውሯል።

“ጉርኒካ” በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከተሳሉ ስዕሎች የጦርነት ጭካኔዎችን በመቃወም ከተሰሩ የጥበብ ስራዎች በጉልህ ተቀምጧል፡፡

በ-ሃይማኖት ወርቁ

ShareTweetShare
Previous Post

35ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች

Next Post

አስከፊው የሱዳን ጦርነት የረሀብ አደጋ ደቅኗል

Related Posts

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ
News

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ

November 13, 2026
16
የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Uncategorized

የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ

October 10, 2026
19
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል
News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

October 9, 2026
16
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ
News

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ

October 8, 2026
33
የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ
News

የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

October 2, 2026
23
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019
Uncategorized

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019

September 27, 2026
23
Next Post

አስከፊው የሱዳን ጦርነት የረሀብ አደጋ ደቅኗል

የአስም በሽታ እና ምልክቶቹ?

የአስም በሽታ እና ምልክቶቹ?

ሰሞነኛ አስገራሚ እና አነጋጋሪ ጉዳዮች

ሰሞነኛ አስገራሚ እና አነጋጋሪ ጉዳዮች

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?