Wednesday, November 18, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Uncategorized

የሰሞኑ ግርምት ጫሪ ክስተቶች

June 7, 2024
in Uncategorized
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ግንቦት 30 2016| NBC ETHIOPIA- በየጊዜው በርካታ አዳዲስ ሁነቶችን ከማስተናገድ ወደሀኋላ ብላ የማታውቀው ዓለማችን እጅን በአፍ የሚያስጭኑ እና እንዲህም አለ እንዴ የሚያስብሉ ክስተቶችን በእየለቱ ታስመለክተናለች።

በአራቱም የአለማችን አቅጣጫዎች የሚገኙ ግለሰቦችም ለመዝናናት ይሁን ዝነኝነት ለማግኘት በሚል የሚቻሉ እና የሚደፈሩ የማይመስሉ ነገሮችን ሲያደርጉ እናስተውላለን፡፡በአለም የድንቃድንቅ መዝገብ ስማቸውን ለማስፈር በርካቶች መስዋዕትነት ይከፍላሉ።

መስዋዕትነቱ በቀላል ድካም ሲያልፍ በአንዳንዶቹ ላይ ደግሞ ለረጅም ጊዜ በአካል እና በአዕምሮ ጤና  ላይ ከፍጸኛ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ይሆናል፡፡

ባስ ሲል ደግሞ ድፍረታቸው እና ለጀብድ ካላቸው ጥልቅ ፍቅር የተነሳ ግለሰቦች የሚከውኑት ተግባራት ሂወታቸውን ሲያሳጣቸውም አስተውለናል፡፡ መነጋገሪያ ለመሆንም ይሁን ለስራ ፈጠራ በርካቶች አዳዲስ ነገሮችን በዕየለቱ ያስመለክቱናል፡፡

ለዛሬም ከሰሞኑን ዓለም ካስተናገደቻቸው አስገራሚ ሁነቶች መካከል የተወሰኑትን መርጠናል።

በመላው ሩሲያ የእግር ኳስ ቀንን በሉዝሂኒኪ ኦሎምፒክ ስፖርት ኮምፕሌክስ ተከብሯል፡፡ ታዲያ የሚያስገርመው ክስተት የተፈጠረው እያንዳንዳቸው 7 ተጫዋች ያላቸው 2 ቡድኖች ያደረጉት ግጥሚያ ነው፡፡ ጨዋታው በእግር ኳስ ታሪክ የዓለማችን ረጅም የሚባለውን 26 ሰዓታትን የፈጀ ሆኗል፡፡

በ26 ሰአታቱ ቆይታ 825 ግቦች የተቆጠሩበት ሲሆን ይህ የእግር ኳስ ጨዋታ ከሰሞኑ ግርምትን የጫረ ክስተት ሆኗል፡፡

እነዚህ ሁለት የሩሲያ የእግር ኳስ ቡድኖች የዓለማችንን ረጅም ሰአት ያስቆጠረ የእግር ኳስ ግጥሚያ በማድረግ ሪከርድ መስበር ችለዋል።

ጨዋታው ቅዳሜ እኩለ ቀን ላይ ተጀምሮ ከ26 ሰአት በኋላ እሁድ ማታ ሊጠናቀቅ ችሏል። ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ በ2014 ሁለት ቡድኖች ለ24 ሰአታት ያህል የእግር ኳስ ጨዋታ በማደረግ ሪከርድ መሰበር ችለው ነበር።

ለተከታታይ 26 ሰአታት የተደረገው ጨዋታው ተጫዋቾች ለሁለት ሰአታት ቀጥ ብለው እንዲጫወቱ እና ከዚያም የስምንት ደቂቃ የመታጠቢያ ቤት እረፍት እንዲወሰዱ ሲደረግ ነበር።

እያንዳንዳቸው 7 ተጫዋች ያላቸው 2 ቡድኖች ያደረጉት ፍልሚያ ይፋዊ የእግር ኳስ ጨዋታ ህግን ባለሟሟላቱ በወርልድ ጊነስ ሪከርድ መመዝገብ አለመቻሉ ተነግሯል፡፡

ማርም ሲበዛ ይመራል እንዲሉ አጉል ቀልዶች ዋጋ ማስከፋላቸው አይቀሬ ነው፡፡ የማህበራዊ ትስስር ገፅ በሆነው ቲክቶክ  በመንገድ ላይ ሰዎችን በማቀፍ ፕራንክ ሲያደርግ የነበረው ቲክ ቶከር በሁለት ወር እስራት መቀጣቱ የሰሞኑ አነጋጋሪ ዜና ሆኗል፡፡

አሁን አሁን ያለ ሰዎች ፍቃድ ሰዎችን በመቅረጽ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የሚለቀቁ ቪዲዮዎች እየተበረታከቱ ነው፡፡

ታዲያ ይህ ድርጊት ያሳሰባት አልጄሪያ ሌሎች ይማሩበታል ያለችውን ውሳኔ  የወሰደች ይመስላል።

መሀመድ ራምዚ ይባላል፡፡  መሀመድ አልጄሪያዊ ሲሆን ቲክ ቶክ በተሰኘው ማህበራዊ ትስስር ገጽ ጎዳና ላይ በሚቀርጻቸው የተለያዩ ተግባራት ብዙ ተከታዮችን ማፍራት ችሏል፡

ታዲያ ይህ ግለሰብ ከሰሞኑ የፈጸመው ድርጊት ብዙዎችን አስቆጥቷል። እስር ቤት እንዲገባም ዳርጎታል፡፡

በመንገድ ላይ በዘፈቀደ ሰዎችን አቅፎ በመያዝ እና ጨዋነት የጎደለው ድርጊት በመፈጸሙ ተከሶ የሁለት ወር እስራት እና የ37,000 ዶላር ቅጣት ተፈርዶበታል።

መሐመድ ራምዚ የተከሰሰበትን ጉዳይ ሲያብራራ በማህበራዊ ትስስር ገጹ የተሰራጩት ተንቀሳቃሽ ምስሎች ሰላምና ፍቅርን ለመስበክ ብቻ ተብለው የተቀረፁ እንደሆነ በማስረዳት ይቅርታ ቢጠይቅም እንደ አለመታደል ሆኖ ተቀባይነትን ማግኘት ሳይችል ወደ እስርቤት ተልኳል፡፡

ከሰሞኑ ከወደ ቻይና የተሰማው መረጃ ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል።በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ እንዲሁም በርዝመቱ በእስያ ተስተካካይ ወደ አላገኘው አስደናቂው የተፈጥሮ ፏፏቴ ስፍራ ያቀና አንድ ቱሪስት በቀረጻ መሃል በስልኩ ያስመለከተው ተንቀሳቃሽ ምስል ግርምትን የጫረ እና ብዙዎችን እያከራከረ ያለ ጉዳይ ሆኗል፡፡

በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወረ ያለው እና መገናኛ ብዙሃኖች እያስመለከቱት ያለው ቪዲዮ ከረጅም ተራራ ላይ የሚወረወረው ፏፏቴ መሃል የውሃ መግፊያ ፓምፖችን አስመልክቷል፡፡

ፏፏቴው ወዳለበት አናት ማቅናት የቻለው የማህበራዊ ትስስር ገጽ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነው ይህው ግለሰው የለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል ፏፏቴው በተፈጥሮ ብቻ አመቱን ሙሉ ሳይቋረጥ ይፈሳል የሚለውን ትርክት የሰበረ ሆኗል፡፡

የቻይና ዩንታይ ፏፏቴ በእስያ ከሚገኙ አስደናቂ የተፈጥሮ ፏፏቴዎች አንዱ እና  በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቱሪስቶች የሚጎበኙት ውብ ስፍራ ነው፡፡ ታዲያ ይህ ተንቀሳቃሽ ምስል ሰዎችን በሁለት ጎራ ያሰለፈ ሆኖ ሰንብቷል፡፡

ግማሾቹ ተንቀሳቃሽ ምስሉ ዘመን አመጣቸሽ በሆነ ቴክኖሎጂ ተቀነባብሮ የተለቀቀ ነው ሲሉ ሌሎቹ ድግሞ እውነተኛ ነው የተፈጥሮ ጥበቃ ባለስልጣናቱ ሲያታልሉን ቆይተዋል በሚል አከራክሯል፡፡

ታዲያ ይህ ጉዳይ ያሳሰበው የዚህ ፏፏቴ አስተዳደር ጉዳዩን ለማርገብ መግለጫ ሰቷል፡፡በመግለጫውም ፏፏቴው የበለጠ አስደናቂ እንዲሆን እና አመቱን ሙሉ ሳይቋረጥ ለጎብኝዎች ጥሩ እይታን እና አስገራሚ ተሞክሮ, ለመስጠት ታስቦ የተደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡

በ- ሀይማኖት ወርቁ

ShareTweetShare
Previous Post

ሩሲያ የፈረንሳይ ዜጋን በስለላ ወንጀል ከሰሰች

Next Post

Related Posts

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ
News

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ

November 13, 2026
21
የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Uncategorized

የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ

October 10, 2026
23
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል
News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

October 9, 2026
20
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ
News

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ

October 8, 2026
37
የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ
News

የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

October 2, 2026
27
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019
Uncategorized

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019

September 27, 2026
27
Next Post

ዩክሬን ሩሲያ ላይ ጥቃት ከፈተች

ዩክሬን ሩሲያ ላይ ጥቃት ከፈተች

የፕሪዝን ብሬክ አስገራሚ እውነታዎች

የፕሪዝን ብሬክ አስገራሚ እውነታዎች

Recent News

ፋኖ ፀረ-ሰላም ኃይል ነው-የቀድሞው የፋኖ አመራር ማርእሸት ፀሐዩ

ፋኖ ፀረ-ሰላም ኃይል ነው-የቀድሞው የፋኖ አመራር ማርእሸት ፀሐዩ

November 18, 2026
በተመድ እውቅና ያገኘው አረንጓዴ አሻራ!

በተመድ እውቅና ያገኘው አረንጓዴ አሻራ!

November 18, 2026
“ማንቸስተር ሁሌም ‘ሰማያዊ’ ሆኖ አይቀጥልም ” ፖቼቲኖ

“ማንቸስተር ሁሌም ‘ሰማያዊ’ ሆኖ አይቀጥልም ” ፖቼቲኖ

November 18, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

ፋኖ ፀረ-ሰላም ኃይል ነው-የቀድሞው የፋኖ አመራር ማርእሸት ፀሐዩ

ፋኖ ፀረ-ሰላም ኃይል ነው-የቀድሞው የፋኖ አመራር ማርእሸት ፀሐዩ

November 18, 2026
በተመድ እውቅና ያገኘው አረንጓዴ አሻራ!

በተመድ እውቅና ያገኘው አረንጓዴ አሻራ!

November 18, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?