በሰኔ ለእይታ የሚቀርቡ ድራማዎች
፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ ሰኔ 01 2016| NBC ETHIOPIA- በፈረነረጆቹ 2024 የተለያዩ ዘውግ ያላቸው ፊልሞች እና ድራማዎች ለተመልካች እየደረሱ ይገኛሉ፡፡ ቢቢሲ በተያዘው የሰኔ ወር ለተመልካቾች እይታ የሚቀርቡ እና የቀረቡ ምርጥ ተከታታይ የቴሌቪዠን ድራማችን በመለየት እስከ 10 ደረጃ የሰጠ ሲሆን ምርጥ 5 የሆኑትን እናስመለክታቹ፡፡ 1. Presumed Innocent

Presumed Innocent እ.ኤ.አ በ1987 ስኮት ቱሮ ከተባለ ልብ ወለድ ላይ ታሪኩ የተወሰደ ሲሆን በወንጀል ምርመራ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ተከታታይ ድራማ ነው፡፡ በአላን ፓኩላ እና ፍራንክ ፒርሰን የፊልሙን ድርሰት ያዘጋጁት ሲሆን ፓኩላ ዳይሬክት አድርጎታል፡፡ አንድ አቃቤ ህግ በአንድ ባልደረባው ግድያ ወንጀል ዋና ተጠርጣሪ በመሆኑ እራሱን ነጻ ለማውጣት የሚያደርገውን ትግል እግር በእግር የሚያሰይ ተከታታይ ድራማ ነው፡፡ ጄክ ጊለንሃል ዋና ገጸ ባህሪውን በመላበስ ድንቅ ብቃቱን ያሳየበት ድራማ ነው፡፡ እጅግ ልብ አንጠልጣይ የሆነው ድራማው በመጪው ሰኔ 12 በApple TV+ ላይ ለተመልካቾች ይቀርባል፡፡ ቢቢሲ ተመልካቾች ቢያዩት ብሎ ካስቀመጠው ድራማዎች መካከል በ5 ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
2. Becoming Karl Lagerfeld

በኢሳዩር ፒሳኒ-ፌሪ፣ ጄኒፈር ሃቭ እና ራፋኤል ባኩዌ የተዘጋጀ እና በፋሽን ኢንዱስትሪ ላይ ያጠነጠነ የፈረንሳይ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ነው ቢካሚንግ ካርል ላገርፌልድ (Becoming Karl Lagerfeld) ድራማው መቼቱን መጀመሪያ በፈረንሳይ፣ ሞናኮ እና ጣሊያን ያደረገ ሲሆን ቀረፃ መካሄድ የጀመረው እ.ኤ.አ በመጋቢት 2023 ነበር፡፡ ዳንኤል ብሩህል የድራማው ዋና ገጸ ባህሪን በመወከል ተጫውቷል። ባለስድስት ተከታታይ የትዕይንት ክፍሎች ያለው ድራማው ሰኔ 7፣ 2024 በDisney+ ለእይታ ቀርቧል፡፡ በ1970 እውቅ የፋሽን ዲዛነር በነበረው ካርል የስራ ህይወቱ እና በፋሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ የሚያጋጥመውን ፈተና ዙሪያ ያጠነጠነ ድራማ ነው፡፡ ድራማው እ.ኤ.አ ከ1972 እስከ 1981 ባሉትን ዓመታት በፋሽን ኢንዱስትሪውን የተፈጠሩ ክስተቶች ቁልጭ አድረጎ የሚያስቀኝ ነው፡፡ ቢቢሲ ተመልካቾች ቢያዩት ብሎ ከመረጣቸው የቴሌቭዥን ተካታታይ ድራማዎች መካካል የአራተኛ ደረጃን አጎናጽፎታል፡፡ 3.Fantasmas

ፋንታስማስ ኮሜዲ ዘውግ ያለው የቴሌቭዥን ድራማ ነው፡፡ ጁሊዮ ቶረስ በዳይሬክቲግ፣ በድርሰት እንዲሁም መሪውን ገጸ ባህሪ በመተወን የተሳተፈበት ተከታታይ ድራማ ነው፡፡ ከሁለት ቀናት በኃላ ሰኔ 7 በአሜሪካ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሆም ቦክስ ኦፊስ ለእይታ ይቀርባል፡፡ ቶሬስ በአንድ አጋጣሚ የጠፋበትን የወርቅ ጉትቻ በተለያዩ መንገድ ለማግኘት ሲሞክር የሚያሰይ ልብ አንጠልጣይ ድራማ ነው፡፡ ውድ የሆነውን ወርቅ ለማግኘት በኒውዮርክ ከተማ በሚያደርገው ፍለጋ የሚያጋጥሙትን አስቂኝ ፣አስፈሪ እና በፍለጋው ወቅት ከሚያገኛቸው ሰዎች ጋር የሚያደርገውን መስተጋብር ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ ድራማው የ3ተኛ ደረጃን ማግኘት ችሏል፡፡
4. Queenie

ቢቢሲ በሰኔ ወር ለእይታ ተወዳጅ እና ምርጥ ብሎ ደረጃ ከሰጣቸው ድራማዎች መካከል የ2ተኛ ደረጃን ሰጥቶታል ኩዊኒ ፡፡ Candice Carty-Williams ከተሰኘው ልብ ወለድ ታሪክ ላይ የተመሰረተ የብሪቲሽ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ነው። ድራማው Further South Productions ከLionsgate Television ጋር በመተባበር ነው እ.ኤ.አ በሰኔ 7 ለእይታ ቀርቧል፡፡
ዲዮን ብራውን ፣ሳሙኤል አድዊሚን እና ቤላህ የድራማውን በዋና ገጸ ባህሪ በመላበስ ተውነዋል፡፡ ኪውን የተባለች የፊልሙ ዋና ገጸ ባህሪ ተጫዋች በፍቅር ለረጅም አመታት አብራወ ከቆየችው ፍቅረኛዋ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በመለያየታቸው የተነሳ የምታሳልፋቸውን አስቸጋሪ እና ውስብስብ ክስተቶችን ስታስተናግድ የሚያሳይ ድራማ ነው፡፡ ድራማው 8ተከታታይ ክፍሎች ያሉት ሲሆን በቀናት ልዩነት ለተመልካች በቻናል 4 ለእይታ ይቀርባል፡፡
4. The Acolyte star wars

አኮላይት ወይም ስታር ዋርስ በመባልም ይታወቃል፡፡ በተያዘው የሰኔ ወር ተመልካቾች እንዲያዩት በአንደኛ ደረጃ የተቀመጠ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ነው፡፡ 180 ሚሊየን ዶላር ወጪ የወጣበት ድራማው እንደ ኤ.እ.አ ከ1977 ጀምሮ በተለያዩ ክፍሎች ለተመልካቾች ሲቀርብ የነበረው የስታር ዋር ተከታታይ ድራማ ክፍል ነው፡፡ ለእይታ የቀረበው ድራማው አንድ ሲዝን ያለው ፊልሙ በውስጡ 2 ክፍሎችን ይዟል፡፡ አክሽን አድቬንቸር ዘውግ ያለው ድራማው በአሜሪካ ፊልም እና የቴሌቪዥን ዳይሬክተር ፣ ፕሮዲዩሰር ፣ ደራሲ በሆነችው ሌስሊ ሄድላነድ ነው፡፡
በዴዝኒ ፕላስ ፊልም ፕሮዳክሽ ለተመልካቾች የቀረበው ድራማው በአሜሪካ የሳይንስ ልብወለድ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ አማንድላ ስተንበርግ ፣ ሊ ጁንግ-ጄ ፣ማኒ ጃሲንቶ እና ሌሎች እውቅ ተዋናዮች በድራማው ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ የድራማው መቼት በለንደን ከተማ እና በሺንፊልድ ስቱዲዮ ሲሆን ከጥቅምት 2022 እስከ ሰኔ 2023 ድረስ ጊዜ ፈጅቶል፡፡ የድራማው ተከታይ ስድስት ክፍሎች በየሳምንቱ የሚለቀቁ ሲሆን በብዙ የፊልም ባለሙያዎች ዘንድ የቀረጻ ስፍራው፣የተዋናዮች ምርጫን ጨምሮ ድራማው የተሰራበት ቅንብር እጅግ የጠዋጣለት እንደሆነ መስክረዋል፡፡












