Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Uncategorized

የዓለማችን ባለፀጎች መኖሪያ ሞናኮ

May 22, 2024
in Uncategorized
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

የዓለማችን ልጥጦች እና ዝነኞች ለምን እና እንዴት ሳይባሉ ያሻቸውን የሚያደርጉባት የዓለማችን ቅንጡዋ ሀገር ናት።

በአለም አቀፍ ደረጃ በማራኪው ገጽታዋ፣ በውብ ቤተመንግስቶቿ፣ በአስደናቂ ሙዚየሞቿ፣ በልዩ የአትክልት ስፍራዎቿ ፣በቅንጡ ሆቴሎቿ ፣በባህር ዳርቻዎቿ እንዲሁም የቅንጡ ህይወት በሚኖሩ ነዋሪዎቿ ይበልጡኑ ትታወቃለች ሞናኮ፡፡

ሞናኮ በመሬት ስፋትም ሆነ በሕዝብ ብዛት በዓለም ላይ ካሉ ትናንሽ አገሮች አንዷ ናት።በምዕራብ አውሮፓ በፈረንሳይ ሪቪዬራ ላይ የምትገኘዋ  ሞናኮ የቆዳ ስፋቷ 2.02 ስኩዌር ኪሎ ሜትር (0.78 ካሬ ማይል) ብቻ ነው። ይህም ዓለማችን ላይ ከቫቲካን በመቀጠል ሁለተኛዋ የዓለም ትንሿ ሀገር ናት ይላሉ በዙሪያዋ የሚወጡ መረጃዎች።

ሞናኮ የዓለማችን ባለጠጎች መኖሪያ ናት።እ.ኤ.አ በ2023 የቅንጦት ህይወት የሚኖርባት ሞናኮ አጠቃላይ የህዝብ ብዛቷ 38,367 ነበር። ከሞናኮ ህዝብ አንድ ሶስተኛ የሚሆነው ሚሊየነር እንደሆነ ይገመታል። በሞናኮ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር የፈሰሰበት የአልማዝ መአድን አጊጠው ቢወጡም ዞር ብሎ የሚያዮት ላይኖር ይችላል ይህ ሞናኮ ነው በቃ የአለም ምርጥ ሀብታሞች የሚምነሸነሹበት ስፍራ።

በሞናኮ የሄሊኮፕተር ጉዞ የተሽከርካሪ ያህል ቀላሉ የመጓጓዣ ዘዴ ነው። ለነጋዴዎች፣ ለታዋቂ ግለሰቦች  እንዲሁም  ለባለጸጋዎች ቀልጣፋ የመጓጓዣ ዘዴ በመሆኑ ሄሊኮፕተር ተመራጭ ነው።

የሄሊኮፕተር አገልግሎቶች ሞናኮን ከፈረንሳይ ኒስ ኮት ዲዙር አውሮፕላን ማረፊያ እና ሌሎች በፈረንሳይ ሪቪዬራ ከሚገኙ መዳረሻዎች ጋር እንዲገናኙ የተደረገ ነው።

የሪል እስቴት ቤቶች  በጣም ውድ ከሆኑባቸው ሀገራት መካከል ሞናኮ ተጠቃሽ ናት። ካለው የመሬት አቅርቦት እጥረት እና ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ እንዲሁም ሀገሪቱ ላይ ባለው ልዩ የቅንጦት ገበያ ምክንያት በዓለም ላይ በጣም ውድ ከሚባሉ ሀገሮች ተርታ እንድትሰለፍ አድርጓታል።

በሞናኮ የእግረኞችን እንቅስቃሴ ለማመቻቸት ነው በሚል በዋና ከተማዋ ውስጥ በተወሰኑ ቦታዎች ነፃ አሳንሰሮች እና መወጣጫዎች አሉ።እነዚህ አሳንሰሮች የሚገኙት ኮረብታዎች ባሉበት አካባቢ ሲሆን ይህም ለተለያዩ የከተማው ቦታዎች ምቹ መዳረሻን ለመፍጠር እና እግረኞች የከተማውን ገጽታ በቀላሉ መጎብኘት እንዲችሉ  ለማድርግ ታስቦ ነው።

Monte Carlo Casino square front day view

በሀገሪቱ ፈጽሞ ከተከለከሉ  ጉዳዮች መካከል ቁማር መጫወት ነው። ይህ ድርጊት በህግ ሳይቀር የተከለከለ ነው፡፡ ይህንን ገደብ መጣል ያስፈለገው ዜጎች የቁማር ሱስ ሊያስከትልባቸው ከሚችለው አሉታዊ ተፅእኖዎች ለመጠበቅ ስለመሆኑ ይነገራል።

ሞናኮ በዓለም ላይ ካሉ ዝቅተኛ ወንጀል ከተመዘገበባቸው ሀገራት አንዷ ናት።ከፍተኛ የሆነ ደህንነት እንዳላት የሚነገርላት ሞናኮ በአማካኝ ለ73 ነዋሪዎች አንድ የፖሊስ አባል አላት።

ሞናኮ ለነጋዴዎች፣ ለታዋቂ ሰዎች እና ለባለሃብቶች ኑሮ ተመራጭ እንድትሆን ያደረጋት ዋነኛ ምክንያት ምንድ ነው ቢሉ የገቢ ታክስ አለማስከፈሏ ነው። የሞናኮ ነዋሪ እስከሆኑ ድረስ ግዛቲቱ ለዓለም አቀፍ ገቢዎች የግል የገቢ ታክስ አትጥልም።

ሞናኮ ህዝቦቿ የአለማችን ከፍተኛ የሞት ጣራ መጠንን የያዙ ናቸው። በአማካኝም 85 ዓመት የእድሜ ጣራ አላት ።የነዋሪዎች አማካይ ዕድሜ ወደ 44 ዓመት አካባቢ ነው, እና 14% የሚሆነው ህዝብ ከ 75 ዓመት በላይ ነው።ይህ የሆነበት ምክንያት በሀገሪቱ ያለው የጤና እንክብካቤ ጥራት፣ ምርጥ የአመጋገብ ስርዓት የሚከተሉ ሃብታሞች የሚኖሩባት በመሆኗ እንደሆነ ይነገራል።

ሞንቴ ካርሎ ካሲኖ በሞናኮ ውስጥ በጣም ታዋቂ፣ የከተማዋ ውበት እና ድምቀት የሆነ ስፍራ ነው።በርካታ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎችም ይህንን ቦታ ለመጎብኘት ወደ ስፍራው ያቀናሉ።

መረጃዎች እንደሚያመላክቱት የአለም ዲታዎች በዚች ሀገር በነጻነት ይኖራሉ፣ በአለም ዙሪያ በምጡቅ አእምሮዎች ዲዛይን የተደረጉ ውድ ምርቶች በዚህች ሀገር አገልግሎት ላይ ይውላል

ስለምትንቀሳቀሱበት ስፍራ ፍጹም ነጻነት ይሰማችሁ ስትል ሞናኮ ድብቅ ካሜራዎች እና አዳኝ የካሜራ ባለሙያዎች ድርሽ እንዳይሉም ከልክላለች፡፡

በ- ሃይማኖት ወርቁ

ShareTweetShare
Previous Post

በሞት ያጣናውን ሰው የሚያገናኘው መተግበሪያ

Next Post

አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

Related Posts

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ
News

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ

November 13, 2026
16
የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Uncategorized

የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ

October 10, 2026
19
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል
News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

October 9, 2026
16
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ
News

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ

October 8, 2026
33
የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ
News

የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

October 2, 2026
23
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019
Uncategorized

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019

September 27, 2026
23
Next Post
አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

ታሪክ ቀያሪው የድሮን ቴክኖሎጂ

ታሪክ ቀያሪው የድሮን ቴክኖሎጂ

አጫጭር የሀገር ውስጥ መረጃዎች

አጫጭር የሀገር ውስጥ መረጃዎች

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?