፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 06 2016| NBC ETHIOPIA- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 26ኛ መደበኛ ስብሰባው የሜዳይ፣ ኒሻንና ሽልማት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለይፋዊ ስራ ጉብኝት አዘርባጃን ገብተዋል፡፡
-የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ በጅግጅጋ ከተማ የተገነባ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካን በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል።
-የኢትዮ ሳት አገልግሎትና ተደራሽነት ከፍተኛ እድገት እያሳየ መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ገለጸ።
-የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ለመማማሪያ መርሐግብር ወደ መዲናዋ ለመጡ መሪዎች ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲስፋፉና ለህጻናት ምቹ እንዲሆኑ የተሰሩ ስራዎችን አስጎብኝተዋል፡፡
-ኢትዮጵያ እንድታመርት ብቻ ሳይሆን ያመረተችውን እንድትጠቀም መንግስት ትልቅ ትኩረት ሰጥቷል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
-የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መከሩ።
– የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የቅርስ ምርምር ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ፡፡
-በአዲስ አበባ ከደረጃ በታች የሚያመርቱ የፕላስቲክ አምራቾች ከድርጊታቸው የማይቆጠቡ ከሆነ ፋብሪካቸው እንደሚዘጋ የከተማው አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አሳሰበ፡፡
-በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዋቻ ከተማ ከ240 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነባ የንፁህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












