፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 07 2016| NBC ETHIOPIA-የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ የቤተሰብ ቀንን ለሁለተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ እያከበረ ይገኛል። “መተሳሰብ እንደ ቤተሰብ፣ለሀገርና ለማህበረሰብ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ሲሆን ዕለቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ30ኛ ጊዜ ይከበራል።

የቤተሰብ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ በተለያዩ መርሀግብሮች እየተከበረ የሚገኘው እለቱ በክልል ከተሞች ትኩረት ተሰጥቶት ያልሰራበት ጉዳይ መሆኑን በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር የሴቶች እና ህፃናት ዘርፍ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አለሚቱ ኡሙድ በመድረኩ ገልፀዋል።

የቤተሰቦችን ደህንነትን ማረጋገጥ፣ በኢኮኖሚ የተደራጁ ከማድረግ እና እርስ በእርሳቸው ያላቸውን ግንኙነት ከማጠናከር አንፃር ክፍተቶች ስለመኖራቸው ተገልጿል። በኢትዮጵያ የቤተሰብ ቁጥር እስከ 20ሚሊየን እንደሚደርስ ይገመታል።
በ-ሀሴት ኃይሉ
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Website – https://nbcethiopia.com/news/
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












