የተወለደው እ.ኤ.አ በፈረንጆቹ የዘመን ቀመር ነሐሴ 16 ፣ 1954 በካናዳ ፣ በካፑስካሲንግ, ኦንታሪዮ ነው። ከልጅነቱ ጀምሮ የሳይንስ ልብ ወለድ አድናቂ የሆነው ካሜሮን በሆሊውድ መንደር ፊልም የመሰራት ትልቅ ህልም ነበረው።
ካሜሮን እድሜው 17 ሲሆን ቤተሰቦቹ ወደ ፉለርተን ካሊፎርኒያ ለመኖር ያቀናሉ እሱም በፉለርተን ኮሌጅ ተመዝግቦ ትምህርቱን ተከታትሏል። ቀጥሎም ካሜሮን ዩኒቨርሲቲ በመግባት የፊዚክስ ትምህርትን አጥንቷል ። ፊልም የመስራት ትልቅ ህልም የነበረው ካሜሮን ከፉለርተን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ከተመረቀ በኋላ የህይወቱ ትልቅ ህልም ለማሳካት ከፅዳት ሰራተኛነት እስከ ከባድ መኪና ሹፌርነት ሰርቷል።

እ.ኤ.አ. በ1978 ካሜሮን የመጀመሪያውን Xenogenesis የተሰኘውን አጭር ሳይንሳዊ ልብ ወለድ ፊልም መሰራት ቻለ ። በመቀጠልም ጄምስ እ.ኤ.አ. በ1984 ወደፊት ስለሚመጣው ሮቦት ሳይንሳዊ ልቦለድ ታሪክ “The Terminator” በመሰራት የስኬት መንገዱን መጻፍ ቻለ።
ከዚህ በኋላ እንደ Aliens (1986) ፣The Abyss እና Terminator 2 (1989) እንዲሁም Judgment Day (1991) የተሰኙ ፊልሞች በስኬት እና በትልቅ በጀት ለህዝብ ማደረስ ቻለ።
እ.ኤ.አ. በ1990 ካሜሮን Lightstorm Entertainment የተባለ የራሱን የፕሮዳክሽን ኩባንያ ማቋቋም ቻለ። ምንም እንኳን ጄምስ ካሜሮን በፊልም ሰሪነት ቢታወቅም ጥልቅ የባህር አሳሽ እና እጅግ በጣም ጥሩ የፊልም ቴክኖሎጂ ፈጣሪ ባለቤት ነው።
ጄምስ ካሜሮን ከሰራቸው በርካታ ፊልሞች ወስጥም እስከዛሬ ድረስ ስሙን በደማቁ ያኖረበት ስራውን እ.ኤ.አ. በ1997 ታይታኒክን (1997) ፃፈ ። ዘመን አይሽሬ እና በብዙ ተመልካቿች ዘንድ የሚታወሰው ታይታኒክ ፊልም ለይታ ከቀረበበት እ.ኤ.አ 1997 ጀምሮ ለ25 ዓመታት ተወዳጅነቱ ሳያጣ መዝለቅ የቻለ ድንቅ ፊልምም መሆን ቻለ።
በፓራማውት ፒክቸርስ እና በ20 ሴንቸሪ ፎክስ ለእይታ የበቃው ይህ ፊልም በጀምስ ካሜሮን ተጽፎ ተዘጋጅቷል። ይህ ፊልምም የተሰራው ዓለማችን ከማትረሳቸው አስደንጋጭ እና አሳዛኝ ክስተቶች መካከል ታይታኒክ የመስጠም አደጋ ተጠቃሽ ነው። ይህ መርከብ በአሰራሩ በትልቀቱ እና በውበቱ መላው ዓለምን ጉደ ያሰኘ እና የሰውን ልጅ እውቀት የፈተነ ታልቅ ግኝት ነበር።

በዚህ እውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራው ታይታኒክ ፊልም ጃክ እና ሮዝ የተባሉ ከተለያየ የኑሮ ደርጃ የመጡ የሁለት ወጣቶች የፍቅር ታሪክ በማስቃኘት ታይታኒክ መርከብ መስመጥን ተከትሎ ያለውን ውጣውረድ ልብ አንጠልጣይ በሆነ ትእይንት ያሳየናል። “ታይታኒክም” ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ያስገኘ የመጀመሪያው ፊልም ነው። ፊልሙም በምርጥ ዳይሬክተር፣ በምርጥ የፊልም አርትዖት እና በምርጥ ምስል የአካዳሚ ሽልማቶችን ጠራርጎ መወሰድ ችሏል። ሥስት ሰአት ከ አስራ አራት ደቂቃ የሚወስደው ይህ ፊልም በአጠቃላይ 111 ሽልማቶችን ወሰዷል።
ሌላኛው በጄምስ ካሜሮን የተጻፈው የ 3D ፊልም ቴክኖሎጂ ፈር ቀዳጅ የሆነው አቫተር ፊልም እ.ኤ.አ በ2009 ለህዝብ እይታ በቃ። ይህም ፊልም ከፍተኛ የተባለለት ወጪ የወጣበት ነው።በዛው ልክም ከፍተኛ ተመልካችን ያገኘ ፊልም ነው አቫተር።
ይህ ፊልም 66 ሽልማቶችን ባለቤት ሲሆን ታዋቂዎቹ የሆሊውድ ፈርጦች ሳም ዎርቲንግተን፣ ዞዪ ሳልዳኛ፣ እንዲሁም እስጢፋኖስ ላንግ በትወና ተሳትፈውበታል።

በመቀጠልም ጄምስ ካሜሮን ከአሜሪካዊ የፊልም ጸሀፊ እና ፕሮዲውሰር ከሆኑት ባል ና ሚስት ሪክ ጃፋ እና አማንዳ ሲልቨር አቫተር ሀልት ጻፈ። ፊልሙም ሥስት ሰአት ከ አስራ ሁለት ደቂቃ ርዝማኔ ያለው ሲሆን በክፍል አንድ ላይ የነበሩ እና አዳዲስ ተዋናዮችን ተሳትፈውበታል።
ይህ ፊልምም ልክ እንደ ክፍል አንድ ሁሉ ብዙ በጀት የፈሰሰበት ፊልም ነው።ፊልሙ ሁሉንም የቦክስ ቢሮ ሪከርዶች በመስበር አስራ አንድ የአካዳሚ ሽልማቶችን ማግኘት ችሏል። የ3D ፊልም ቴክኖሎጂን ፈር ቀዳጅ የሆነው አቫታር ፊልምም ከ (2009) እስከ 2019 ድረስ ከፍተኛ ገቢ ያስመዘገበው ፊልም ነው።
ጄምስ ካሜሮን የፊልም ዳይሬክተር፣ የፊልም ፕሮዲዩሰር፣ የስክሪን ጸሐፊ፣ ፈጣሪ፣ ተዋናይ፣ የፊልም አርታዒ፣ ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያ፣ የቴሌቪዥን አዘጋጅ እንዲሁም የበርካታ ጥምር ሞያዎች ባለቤት ነው። በሆሊውድ የፊልም ኢንደስትሪ ተጽኖ ፈጣሪ መሆን የቻለው ጄምስ ካሜሮን አጠቃላይ የሀብት መጠኑ 800 ሚሊዮን ዶላር ነው።
በአሁኑ ጊዜ ጄምስ ካሜሮን በሆሊዉድ እጅጉኑ ተፈላጊ ከሆኑት ዳይሬክተሮች መካከል ቁጥር አንድ ነው።
ሰዎች ፍጽም ሰው ነህ ይሉኛል፤ እኔ ግን እንዲህ አይደለሁም። ትክክል ነኝ። ትክክል እስኪሆን ድረስ አንድ ነገር አደርጋለሁ፣ ከዚያም ወደሚቀጥለው ነገር እሄዳለሁ። ሲልም ይናገራል።
በ-ሀይማኖት ወርቁ












