፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 06 2016| NBC ETHIOPIA- የኢትዮ-ብራዚል የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም በብራዚል ሳኦ-ፖሎ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ፎረሙን ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ የብራዚል ኤምባሲ እና በብራዚል የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጀው፡፡

በፎረሙ ላይ በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ጣፋ ቱሉ፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴዔታ ፍስሐ ይታገሱ ፣ የብራዚል የንግድ የኢንዱስትሪና አገልግሎት ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሃላፊ ማርሲዮ ኤልያስ ሮዛ እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡ከዚህ ባለፈም ከ250 በላይ ከኢትዮጵያ እና ብራዚል የተወጣጡ ባለሀብቶች እና ኩባንያዎች መሳተፋቸው ተገልጿል።
ፎረሙ ኢትዮጵያን የብራዚል ባለሃብቶችና ኩባንያዎች ዋነኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻ በማድረግ ረገድ ትልቅ አበርክቶ እንደሚኖረው ተጠቅሷል፡፡

በተለይም በግብርና እና አግሮፕሮሰሲንግ፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በጨርቃጨርቅና በሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች ያለውን ሰፊ ዕድል መጠቀም ያስችላል ተብሏል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች ከብራዚል አቻዎቻቸው ጋር ትስስር ለመፍጠር እንዲሁም የሀገራቸውን ምርቶች በብራዚል ገበያ በስፋት ተደራሽ ማድረግ እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












