፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 18 2016| NBC ETHIOPIA- የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ሲከናወኑ ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ መድን፣ ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ይጫወታሉ፡፡
-የኢትዮ ኤሌክትሪክ እግር ኳስ ክለብ በከፍተኛው ሊግ አምስት ጨዋታዎች እየቀሩት ወደ 2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል፡፡
-የባየር ሙኒክ ደጋፊዎች የክለቡ አሰልጣኝ ቶማስ ቱኸል በክለቡ የአሰልጣኝነት ኃላፊነት እንዲቀጥሉ ድምፅ እያሰባሰቡ ናቸው ተብሏል።
-ብራዚላዊቷ የእግር ኳስ ኮከብ ማርታ ቪዬራ ዳ ሲልቫ በተያዘው የውድድር ዓመት ከእግር ኳስ እንደምትገለል አሳውቃለች፡፡
-የቼልሲ ተጨዋች ኮል ፓልመር ከህመሙ አገግሞ ወደ ልምምድ መመለሱን አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ አረጋግጠዋል።
-ናፖሊ የ24 ዓመቱን ካናዳዊ አጥቂ ጆናታን ዳቪድን ከሊል የማስፈረም ጥረት መጀመሩን ካልቺዮሜርካቶ ዘግቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












