፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 14 2016| NBC ETHIOPIA-
የፊት ቆዳችንን ጤና ለመጠበቅ አንዱ እና ዋነኛው መንገድ ቆዳችንን ከሃይለኛ ጸሀይ መከላከል ነው፡፡ በብዘት ለጸሀይ የተጋለጠ ቆዳ የመሸብሸብ እና ለሌሎች የቆዳ ችግሮች የተጋለጠ ይሆናል ፤ ስለዚህም ከጸሃይ የመከላከያ ቅባቶችን ፣ ዣንጥላ እና ለጸሃይ የማያጋልጡ አይነት አለባበሶችን በመልበስ መከላከል ይቻላል፡፡
![]()
በምግባችን ውስጥ አትክልቶችን እና ፍራፍሬዎችን ማዘውተር ለቆዳ ጤንነት ወሳኝ ነው፡፡
ቆዳችን እንክብካቤ ይፈልጋል የምንጠቀምባቸው ሳሙናዎች ፣ ቅባቶች እና የጺም መላጫ ቁሳቁሶችን ለቆዳችን ተስማሚ መሆናቸውን በሚገባ ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡
ሲጋራ ማጤስ እንደሌሎች የሰውነታችን ክፍሎች ሁሉ ቆዳችንንም ይጎዳል፡፡ ሲጋራ ማጤስ ቆዳን እንዲሸበሸብ በማድረግ ያለ እድሜአችን ያረጀ ገጽታን ሊያላብሰን ስለሚችል ማስወገድ ይኖርብናል፡፡
ከልክ ያለፈ ጭንቀት እና ውጥረት በቆዳችን ላይ ለሚወጡ እንደ ብጉር ላሉ እና ለሌሎች የቆዳ በሽታዎች ስለሚያጋልጡን አእምሯችንን ከጭንቀት መጠበቅ አለብን።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












