፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 07 2016| NBC ETHIOPIA-በግብጻውያን የስልጣኔ ታሪክ ወይንም ኢጅብሺያን ሲቪላይዜሽን ሲነሳ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፤ በሀገሬው ህዝብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ ተሰጥቷቸው እና ተጠብቀው በመቆየታቸው ታሪካዊ ቀለማቸው ሳይጠፋ ዛሬም በየአመቱ ከ14 ሚሊዮን በላይ በሆኑ ጎብኚዎች ይጎበኛሉ፡፡ ጥንታዊ የግብፅ ፒራሚዶች
ለእይታ ማራኪ ከመሆናቸው በላይ በዘመናዊው አርኪኦሎጂ፣ ሥነ-ሕንፃ እና ሥነ ጥበብ መነሻ እንደሆኑም ይታመናል፡፡
ፒራሚዶቹ ከክርስቶስ ልደት በፊት ባሉት ከ2700 እስከ 1500 ጊዜያት፣ ሳይገነቡ እንዳልቀረ የአርኪዮሎጂ ጥናት ባለሞያዎች ይገልጻሉ፡፡
የግብጻውያን ነገስታት ወይንም ፈርኦኖች ከሞት በኋላ ለሚኖራቸው ህይወት የሞተ አካላቸውን ተንከባክቦ ለማቆያ ይጠቀሙበት እደነበርም ይታመናል፡፡ስፍራው እስካሁንም በጥናት ያልተደረሰባቸውን እና ያልተገኙ ታሪኮችን ሰንዶ እንደያዘ ይነገራል፡፡

በቀደሙ ጊዜያት በነበሩ የኪነህንጻ ባለሞያዎች እንደተገነቡ የሚነገርላቸው ፒራሚዶቹ በሚሊየን በሚቆጠሩ የኖራ ድንጋዮች እና ሌሎች ማዕድናት እንታነፁ ይገለጻል፡፡ከአንድ 100 በላይ ከሚልቁት ጥንታዊ የግብጻውያን ፒራሚዶች መካከል በግዝፈቱ በቀዳሚነት ስለተቀመጠው ‹‹ጊዛ›› የተሰኘው ታላቁ ፒራሚድ እንንገራችሁ፡፡
የኩፉ ፒራሚድ ወይም የቼፕስ ፒራሚድ በመባልም ይታወቃል፡፡ በ4ኛው ክፍለ ዘመን ለነበረው ንጉስ ፈርኦን ኩፉ መቃብርነት ያገለገለ እንደነበር ይነገርለታል፡፡ ፒራሚድ በሰሜን ግብፅ አል-ጂዛህ አቅራቢያ በአባይ ወንዝ በስተምዕራብ ባለው ድንጋያማ ቦታ ላይ መገኛውን አድርጓል።
እንደ አውሮፓውያ አቆጣጠር በ1925 አርኪዮሎጂስቶች የኩፉ እናት ንግሥት ሄቴፌረስ ይህንን ስፍራ ትጠቀምበት እና እርሷ ካለፈች በኋላ ለልጇ ኩፉ አስተላልፋ እንዳለፈች የሚያሳይ መረጃ ከስፍራው ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡
487 ጫማ ወይንም 147 ሜትር ርዝማኔ ያለው ፒራሚዱ ለ3800 አመታት ያህል በሰዎች ከተገነቡ ኪነህንጻዎች መካከል የአለማችን ረዥሙ በመሆን ቆይቷል፡፡

የጊዛ ፒራሚድ ከ 2.3 ሚሊዮን በላይ ጡቦች በመገጣጠም የተገነባ ሲሆን፣ በጠቅላላው 6 ሚሊዮን ቶን እንደሚመዝንም ይገመታል፡፡
የጥናት ባለሞያዎች እንደሚያምኑት ግንባታው 20 አመታት የፈጀ ሲሆን፣ ከ 20 ሺ የሚልቁ ባለሞያዎችን ሳይሳተፉበት አልቀረም፡፡ከተለያዩ አካባቢዎች እነዛን ትላልቅ ጡቦች በማጓጓዝ ፤ፈታኝ የሆነውን እንዴት ማሳለጥ እንደተጫለ ግን እስካሁንም በተመራማሪዎች ሊደረስበት ያልቻለ ምስጢር ሆንዋል፡፡
ከ4500 አመታት በላይ እንዳስቆጠረ የሚነገርለት የጊዛ ሙዚየም ለግብጻውያን የዘመኑ ስልጣኔያቸው ምልክት ከመሆኑ ባሻገር በቱሪስት መስህብነቱ በየአመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጎብኚዎችን ይስተናገዱበታል፡፡
ከሰባቱ የአለማችን ጥትንዊ እና አስደናቂ ቅርሶች መካከል የሚገኘው ግዙፉ የጊዛ ፒራሚድ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 1979 አመተ ምህረት በዩኔስኮ የአለም ቅርስነት መዝገብ የአለማችን ግዙፉ እና ጥንታዊው ኪነህንጻ በመሆን ተመዝግቧል፡፡
በ-የአብስራ ሚሊዮን












