፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 08 2016| NBC ETHIOPIA-በኢንዶኔዥያ ታምቦራ ተራራ የተከሰተው የእሳተ ጎመራ ፍንዳታ ባለፉት 10,000 ዓመታት ውስጥ በምድር ላይ ከተፈጠሩ የተፈጥሮ ክስተቶች መካካል እጅግ አጥፊው እና በርካታ ውድመትን ያስከተለ ተብሎ በታሪክ መዛግብት ተከትቧል፡፡ ታምቦራ በኢንዶኔዥያ ደሴቶች ምሥራቃዊ ጫፍ በሱምባዋ ደሴት የሚገኝ ተራራ ነው፡፡
ከ13,000 ጫማ በላይ ከፍታ ያለው ይህ ተራራ ልክ እ.ኤ.አ በ1815 ከ209 አመታት በፊት ነበር የዓለም አስከፊውን የእሳተ ጎመራ ፍንዳታን ያስተናገደው፡፡ ፍንዳታው እጅግ ከባድ በመሆኑም 100 ኪዩቢክ ኪሎ ሜትር ጋዞችን፣ አቧራ፣ አለትን ወደ ከባቢ አየር በፍንዳታው ለቆል፡፡
ከፍተኛ ውድመት ያስከተለው ይህ ፍንዳታ በአከባቢው የነበሩ ደንኖችን ሙሉ ለሙሉ ወደ አመድነት ቀይሯል፡፡ ኑሮአቸውን በደሴቱቱ ዙሪያ አድርገው የነበሩ 100ሺየሚጠጉ ሰዎችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ህይወት ቀጥፏል፡፡ በሱምባዋ ደሴት 10,00 ሰዎች በፍንዳታው የሞቱ ሲሆን በቀጣዮቹ ወራትም በአካባቢው በተከሰተው የምርት እጥረት እና በሽታ ከ80,000 በላይ ሰዎች በረሃብ እና በሽታ ሞተዋል፡፡

የዘርፉ ተመራማሪዎች የእሳተ ገሞራው ፍርስራሽ ለብዙ ወራት የምድር ክፍሎች እንዴት እንደሸፈነው ጥናት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ የሰብል ውድመትን፣ረሃብ እንዲሁም ወረርሽኝን ከእሳተ ጎመራው ፍንዳታ በኃላ ያስተናገደቻቸው ችግሮች ነበሩ፡፡
የአየር ንብረት ጠበብት ታምቦራ በ1816 አብዛኛውን ሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ ላጋጠመው ያልተጠበቀ ቅዝቃዜ ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ የታምቦራ ፍንዳታ በ900 ማይል ርቀት ላይ ከሚገኘው የክራካታው እሳተጎመራ ፍንዳታ በአሥር እጥፍ የላቀ እንደነበር ታሪክ ያወሳል፡፡ የታምቦራ የእሳተ ጎመራ ፍንዳታ ከተሰተ ከ68 አመታት በኃላ እ.ኤ.አ በ1883 ነው የክራካታ ፍንዳታን አለም ያስተናገደችው፡፡
ለብዙሀን ህይወት መጥፋት ምክንያት ከሆነው የ1815 ፍንዳት የክራካታው እሳተ ጎመራ ፍንዳታ በሰፊው የዓለም ህዝብ የሚታወቅ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ቴሌግራፍ ከተፈለሰፈ በኋላ ክስተቱ በፍጥነት በዜና በመሰራጨቱ ነበር፡፡ የታምቦራ ፍንዳታ በታሪክ ውስጥ የተከሰቱት የተፈጥሮ ክስተቶች ምን ያክል ምድርን፣ ከባቢ አየርን እና ነዋሪዎችን እንደሚጎዳ አመላካች እንደሆነ የዘርፉ ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡ የአለም ሙቀት መጨመር እና የከባቢ አየር መከላከያ የኦዞን ንጣፍ መጥፋትን የመሳሰሉ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች የእነዚህ ተፈጥሮአዊ አደጋች በተደጋጋሚ መከሰት ውጤት ናቸው፡፡
የታምቦራ ፍንዳታ እሳተ ገሞራ ፍንዳታ የተለቀቀው ጭስ በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት አስከፊ የሆነ የአየር ብክለት እንዲከሰተ ማድረጉ ይነገራል፡፡ ትናንሽ የአለት ቅንጣቶች ወደ መካከለኛው ከባቢ አየር በመለቀቃቸው የፀሐይ ጨረር ወደ ምድር እንዳይደርስ መከልከሉን የዘርፉ ጠብብቶች ያስረዳሉ፡፡
በዚህም ወደ ምድር የሚደርሰው የፀሐይ ብርሃንን በመቀነስ በዝቅተኛ ከባቢ አየር ላይ ቅዝቃዜ እንዲፈጥር አድርጓል፡፡ ይህም የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ የአለም ሙቀት መጠን በአማካኝ በ3°ሴ (5.4°F) ቀንሶታል።
የታምቦራ ተራራ እሳተ ጎመራ ከመፈንዳቱ ጥቂት ዓመታት በፊት ሌሎች የእሳተ ገሞራ ፍንዳታዎችን በኢንዶኔዥያ እና አከባቢው ሲስተዋል እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ይመሰክራሉ፡፡

በ1812 እና 1813 መካከል ትንንሽ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታዎች በሪዩኩ ደሴቶች፣ ኢንዶኔዥያ እና ካሪቢያን አካባቢዎች የተከሰቱ ሲሆን በ1814 በፊሊፒንስ የማዮን እሳተ ገሞራ ሌላኛው እሳተ ገመራ ፍንዳታ ነበር፡፡
በኢንዶኔዥያ የተከሰተው ይህ የተፈጥሮ አደጋ ያስከተለው ቀውስ በሀገሪቷ እና በዙሪያዋ ባሉ ሀገራት ብቻ አልነበረው፡፡ በአውሮፓ በተለይም በ1816 የዝናብ መጠን እየጨመረ በመምጣቱ የስንዴ፣ የአጃ እና የድንች ሰብሎች ከጥቅም ውጪ እንዲሆን አድርጓል፡፡ በዚህም ረሃብ እና በሽታን አስከትሏል። የታይፈስ በሽታ ከ40ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ለህልፈተ ዳርጓል፡፡
የታምቦራ ተራራ ፍንዳታ በእስያ አህጉር የራሱን መጥፎ አሻራ አሳርፏል፡፡ ከህንድ በስተምስራቅ በሚገኘው የቤንጋል የባህር ወሽመጥ አካባቢ ያለውን የአካባቢ ሁኔታ እና ስነ-ምህዳር ላይ ተፅዕኖ በማሳደር የቤንጋል ኮሌራ እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል፡፡በሽታውም በፍጥነት በመስፋፋቱ እስከ 1823 ድረስ በዘለቀው ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ በአሥር ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ገደለ።
የእሳተ ገሞራው ፍንዳታው በአርክቲክ ውቅያኖስ ውስጥ ያለውን ንፋስ እና ሞገድ በማስተጓጎል የበረዶ ግግሮችን ሰባብሯ፡፡ መርከበኞች በአትላንቲክ እና በፓሲፊክ ውቅያኖሶች መካከል ያለውን አቋራጭ መንገድ ለመጠቀም ፍለጋ ተያይዘው ነበር፡፡
እ.ኤ.አ. በ1816 በአሜሪካ በተከተው ከፍተኛ ቅዝቃዜ የምግብ ዋጋ በፍጥነት ሁኔታ ጨምሯል፣ ይህም ምዕራባውያን ወደ ሌሎች ሀገራት እንዲፈልሱ አድርጓል፡፡ የታምቦራ ተራራ ፍንዳታ በ1819 ሲከሰት አሜሪካ የመጀመሪያው ግዙፍ የኢኮኖሚያዊ መዋዠቅን ያስተናገደችበት አመት ሆኖ አልፏል፡፡
ከ209 አመታት በፊት ሚያዚያ 3 እ.ኤ.አ በ1885 የተከሰተው የእሳተ ጎመራ ፍንዳታ የዓለምን ማህበራዊ ተፈጥሮአዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ስነ ምህዳር ያዘበራረቀ ክስተት ሆኖ አልፏል፡፡












