፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 18፣ 2016| NBC ETHIOPIA-በዛሬው ዕለት ለሚካሄደው በአዲስ አበባ ከሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር መርሐግብር ጋር ተያይዞ ከ5፡00 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም መሰረት፤
– ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅ/ኡራኤል ቤ/ክርስቲያን
-ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ
-ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ለከባድ መኪናዎች አጎና ሲኒማ፤ለሌሎች ተሸከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል፡፡
-ከጦር ኃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሸከርካሪዎች በተለምዶ አጠራሩ ክቡ ባንክ አካባቢ
– ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሐራምቤ መብራት ላይ
-ከ4 ኪሎ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛው ላይ፡፡
-ከአዋሬ አካባቢ በካሳንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ኢንተርኮንትኔታል አካባቢ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ የኢፍጠር ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ዝግ የሚደረጉ ይሆናል፡፡
በተጨማሪም በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅመ ሰዓታት ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ ሲሆን ኅብረተሰቡ መርኃ ግብሩ በሠላም ተጀምሮ በሠላም እንዲጠናቀቅ ለፀጥታ አካላት ተባባሪ እንዲሆንና ማንኛውም ዓይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በፖሊስ የመረጃ ስልኮች 0111 11 01 11 እና ነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወልና መረጃ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ የፀጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












