፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 17፣ 2016| NBC ETHIOPIA-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በኢትዮጵያ ፈጠራ እና የእውቀት መሠረት ያለው ኢኮኖሚ ለማደርጀት ያለመ ነው ሲሉ ገለጹ።
-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ መጋቢት 6፣ 2016 ዓ.ም ሌሊት በተፈጠረ ችግር ምክንያት 801,417,747.81 ብር ያላግባብ ተወስዶ እንደነበር እና 622.9 ሚሊዮን ብር ማስመለስ መቻሉ ተገልጿል፡፡
-የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደገለፁት ችግሩ በተከሰተበት ቀን ከምሽቱ
3፡38 ጀምሮ እስከ ሌሊቱ 8፡45 ድረስ በ25,761 ሂሳቦች አማካኝነት 238‚293 ህገወጥ ግብይቶች ተከናውነዋል፡፡
-የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ላይ የመስክ ምልከታ ማካሄድ ጀመረ፡፡
-በምዕራብና ምሥራቅ ሐረርጌ ዞኖች በምክክር መድረኩ የሚሳተፉ ተወካዮች ልየታ እየተከናወነ ነው ተባለ፡፡
-በኢትዮጵያ ከሚነገሩና ከተመዘገቡ 76 ቋንቋዎች 51ዱ የትምህርት ቋንቋ ሆነዋል ተባለ፡፡
-የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሰብዓዊ አገልግሎትና ዘላቂ ልማትን ያጣመረ ፖሊሲ ስራ ላይ አዋለ፡፡
-በመዲናዋ 300 ኪሎ ሜትር የመንገድ ዳር ውሃ ፍሳሽ ቱቦዎችን በአዲስ የመተካትና የማፅዳት ሥራ መከናወኑ ተገለጸ፡፡
-በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ እና አካባቢው ያሉ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የሚያደርግ የ14 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።
-የቻይናው ዌንዡ ኒክሲን ትሬዲንግ ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወረቀት የማምረት ፍላጎት እንዳለው ተገለጸ።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
– https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












