አዲስ አበባ | መጋቢት 12፣ 2016| NBC ETHIOPIA – የብራዚል ፍርድቤት የቀድሞው እግር ኳስ ተጨዋች ሮቢኒሆ፣ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል በጣልያን አገር የተፈረደበትን የ9 ዓመት እስራት በብራዚል እንዲታሰር ወስኗል።
የ40 ዓመቱ የቀድሞ አጥቂ በ2013 ለኤ ሲ ሚላን እየተጫወተ ሳለ በአንድ የ22 ዓመት አልባንያዊ ሴት ላይ በቡድን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጽሟል በሚል ክስ የጣልያን ፍ/ቤት በ2017 የ9 ዓመት እስራት እንደፈረደበት ይታወሳል።
ይሁንና ብራዚል ዜጋዋን አሳልፋ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኗ ጣልያን ፍርዱ ወንጀለኛው በሚኖርበት አገር እንዲፈጸም ስትወትውት ቆይታለች።
ጥያቄዋ ተቀባይነት አግኝቶ የብራዚል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትላንትና በዋለው ችሎት፣ የቀድሞ የሪያል ማድሪድ፣ማንችስተር ሲቲና ሚላን አጥቂ ሮቢኒሆ በጣልያን የተፈረደበት የ9 ዓመት እስራት በብራዚል እንዲፈጸም ዉሳኔ አሳልፏል።
የተከሳሽ ጠበቆች ለብራዚል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ እንደሚሉ አስታውቀዋል።
በዚህም የይግባኝ ክርክሩ እስኪጠናቀቅ ድረስ ደንበኛቸው ከእስር ነጻ ሆኖ ይቆያል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












