አዲስ አበባ | መጋቢት 12፣ 2016| NBC ETHIOPIA -በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የንግስት እሌኒ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አንዲት እናት ሁለት ራስ ቅል ያለው ልጅ በሰላም ተገላግላለች።

አምስት ልጆች ያሏት እናት ከአንገቱ በታች የተያያዘ ሁለት ራስ ያለው ሆኖ የተወለደው ሕፃን ስድስተኛ ልጇ ነው፡፡
እናትም እንዲህ ዓይነት ክስተት መኖሩን ሳታውቅ ቆይታ ለህክምና ከመጣች በኋላ ያወቀች ሲሆን፤ በሆስፒታሉ ሃኪሞች እርዳታ በመለስተኛ ቀዶ ሕክምና በሰላም ተገላግላለች፡፡
በትክክለኛ የእርግዝና ወራት ቆይታ የተወለደው ባለ ሁለት ራስ ሕጻን አራት ነጥብ ሁለት ኪሎ ግራም ይመዝናል፡፡
የተወለደው ህጻን አሁን ላይ ጤንነት ችግር ባይኖረውም ወደፊት አፈጣጠሩ እክል ሊፈጥርበት እንደሚችል አመላካች ነገሮች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
ነገር ግን ተጨማሪ ምርመራዎች በማስፈለጋቸው የሐኪሞች ቡድን ምርመራና ክትትል በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












