-የአፍ ንጽህናን መጠበቅ

ቢያንስ በቀን ሁለት ጊዜ ጥርስዎን ይቦርሹ እና ምላስዎን ማፅዳትን አይርሱ።
-ፍሎስ ያድርጉ

በጥርሶቻችን መካከል የተሰገሰጉ ቆሻሻ በፍሎስ በማስወገድ እና የቆሻሻ ክምችት እንዳይፈጠር ለመከላከል።
-ውሃ መጠጣትን ያዘውትሩ

ውሃ ለሰውነትዎ ብቻ ሳይሆን ለትንፋሽዎ አስፈላጊ ነው።
-ከስኳር ነፃ የሆነ ማስቲካ ወይም ሚንት መጠቀም

ተፈጥሯዊ የአፍ ማጽጃ የሆነውን ምራቅ ማምረት ያበረታታሉ።
-መጥፎ የአፍ ጠረን የሚያስከትሉ ባክቴሪያዎችን የሚዋጉ ፕሮባዮቲክስ ስለሚይዙ እንደ እርጎ እና አይብ ያሉ የወተት ተዋጽኦዎችን ይጠቀሙ።
-ከዕፅዋት የተቀመሙ ሻዮችን መጠቀም
አንድ ኩባያ ተፈጥሯዊ ትንፋሽ የማደስ ባህሪያት ካላቸው ዕፅዋት የተቀመመ ሻይ እንደ ፔፔርሚንት ወይም ኮሞሜላን መጠጣት።
-በጥሬ መበላት የሚችሉ አትክልቶች መመገብ

እንደ ሴሊሪ እና ካሮት ያሉ ጥሬ አትክልቶች ጥርስዎን ለማጽዳት እና ትንፋሽን ለማደስ ይረዳሉ።
-ጠረን የሚያስከትሉ ምግቦችን ይቀንሱ

ከማህበራዊ ዝግጅቶች በፊት ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት እና ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን ያስወግዱ።
-መደበኛ የጥርስ ምርመራዎች ያድርጉ

ማንኛውንም መሰረታዊ ችግሮችን ለመፍታት እና ጥሩ የአፍ ጤንነትን ለማረጋገጥ የጥርስ ህክምና ያድርጉ።












