አዲስ አበባ | መጋቢት 12፣ 2016| NBC ETHIOPIA -በደቡባዊ አፍጋኒስታን ካንዳሃር ከተማ በሚገኝ ባንክ በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አስራ ሁለት የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል ሲሉ የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል።

ታሊባን እ.ኤ.አ በነሀሴ 2021 በአሜሪካ የሚደገፈውን መንግስት በማስወገድ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ በአፍጋኒስታን የቦምብ ፍንዳታ እና የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቶች ቁጥር እንደቀነሰ ይነገራል። ሆኖም በርካታ የታጠቁ ቡድኖች ISISን ጨምሮ አሁንም ለሀገሪቱ ስጋት እንደሆኑ ያስነበበው ሲ ጅ ቲ ኤን ነው ።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












