አዲስ አበባ | መጋቢት 09፣ 2016| NBC ETHIOPIA -ፓኪስታን እና አፍጋኒስታን ግጭት ውስጥ መግባታቸው ተገለጸ፡፡ የፓኪስታን ተዋጊ ጀቶች በአፍጋኒስትን ድንበር አካባቢ ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ ስምንት ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ነው ታሊባን ጥቃት የከፈተው፡፡

በጥቃቱ አምስት ሴቶች እና ሶስት ህጻናት ህይወታቸውን አጥተዋል ተብሏል፡፡ታሊባን ውጤቱ የከፋ ሊሆን ይችላል ሲል በፓኪስታን ኃይሎች ላይ ዝቷል፡፡
የታሊባን ቃል አቀባይ ጉዳዩን በማውገዝ የግደሌሽነት ጥቃት እና የአፍጋኒስታንን ሉዓላዊነት የሚጋፋ ነው ሲሉ ተችተውታል፡፡
በፓኪስታንና አፍጋኒስታን መካከል የድንበር ውጥረት እየተባበሰ የመጣው ታሊባን ከሶስት ዓመታት ዳግም ስልጣን ከያዘ ወዲህ ካቡል እና ኢስላማባድ ልዩነታቸው እየሰፋ መጥቷል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












