አዲስ አበባ | መጋቢት 10፣ 2016| NBC ETHIOPIA -ክርስትያኖ ሮናልዶ የፊታችን ሀሙስ ከስዊድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ከሚያደርገው የፖርቱጋል ስብስብ ዉጭ ሆኗል።
የ5 ጊዜያት የባሎን ደ’ኦር አሸናፊው ሮናልዶ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ከሳምንት በፊት ይፋ ባደረጉት 32 ተጨዋቾችን በያዘው ጊዜያዊ ስብስባቸው ዉስጥ ተካትቶ እንደነበር ይታወሳል።

ይሁንና ትላንትና የመጨረሻ 24 ተጨዋቾቻቸውን ሲያሳውቁ አንጋፋውን አጥቂ አላካተቱም። ኢ ኤስ ፒ ኤን እንደዘገበው፣ አሰልጣኙ ሮናልዶን ከስብስባቸው ዉጪ ያደረጉት ከቤተሰቦቹ ጋር የሽርሽር ጊዜ ላይ መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ዕረፍት ለመስጠት ብለው ነው።
ስፔናዊው አሰልጣኝ ከሮናልዶ በተጨማሪ ለዲኦጎ ዳሎት፣ጆዋኦ ካንሴሎ፣ ዳኒሎ ፔሬራ፣ ኦታቪዮ፣ሩቢን ኔቨስ፣ ቪቲኒሃ፣ ጆዋኦ ፍሊክስና ሌሎችም በርካታ የዋናው ቡድን ተጨዋቾች ዕረፍት ሰጥተዋል።
ሮናልዶ መጋቢት 17 ከስሎቬኒያ ጋር በሚያደርጉት የወዳጅነት ጨዋታም አይሰለፍም። ክለቡ አል- ናስር መጋቢት 21 ከ አል- ታይ ጋር ላለበት የሊግ ጨዋታ ዝግጅት ማድረግ ስላለበት ነው የብሔራዊ ቡድን ጨዋታው የሚያልፈው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












