አዲስ አበባ | መጋቢት 10፣ 2016| NBC ETHIOPIA -የኢዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከፋሪስ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ጋር በቴክኖሎጂ እና በስራ ፈጠራ ዘርፍ ላይ ለመስራት የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።
የመጀመሪያው እራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለቀጣይ አምስት አመታት ተቋሙ ካዘጋጀው የስራቴጂክ እቅድ መካከል ተማሪዎችን ከመደበኛው የመማር ማስተማር ሂደት ባለፈ ያላቸውን እምቅ አቅም እንዲያወጡ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል አንዱ ነው።

በዚህም በተለያዩ የትምህርት መስክ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ዘርፍ እና በስራ ፈጠራ ላይ እገዛ ለማድረግ እና የገበያ ትስስር ለመፍጠር በማለም ስምምነቱ መካሄዱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ገልፀዋል።
ለሚቀጥሉት አምስት አመታት ስምምነቱ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን በማንኛውም የትምህርት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ እና በቴክኖሎጂ እንዲሁም በፈጠራ ላይ ክህሎት ያላቸው ተማሪዎች ድጋፉን የሚያገኙ ይሆናል ተብሏል።
የፋሪስ ቴክኖሎጂ ግሩፕ መስራች እና ስራ አስፈፃሚ ኤልያስ ይርዳው የተለያዩ ጥናታዊ ምርምሮችን በማድረግ የራስ ችግርን በራስ ለመፍታት እና ከሀገር አልፎ በዓለም ገበያ ላይ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎቹ እንዲቀርቡ እንደሚደረገ ገልጸዋል።
በ- ሃሴት ሀይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












