፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 06፣ 2016| NBC ETHIOPIA -የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የተሾሙ የ6 ሀገራትን አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ።
-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሞሪታንያ ኢስላሚክ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ እና የትብብር ሚኒስትር ዶክተር ሞሃመድ ሳሌም ኦልድ ሜርዙግ ጋር ተወያይተዋል።
-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኡጋንዳ ሪፐብሊክ የፍትሕ እና የሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ኖርበርት ማኦ ጋር ተወያዩ፡፡
-በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሥር የሚገኘው የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ለምርምር ግብዓትነት የሚውሉና የተለያየ ፋይዳ ያላቸው ቅርሶችና ሥጦታዎችን ተረከበ።
-የአድዋ ድል መታሰቢያ ከነገ ጀምሮ ለህዝብ ጉብኝት ክፍት እንደሚሆን ተገለጸ።
-የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ የአባላት ኮንፈረንስ ከነገ ጀምሮ እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
-የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከሩዋንዳው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ዓለምአቀፍ ትብብር ሚኒስትር ቪንሴንት ብሩታ(ዶ/ር) እና ከአልጄሪያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አታፍ ጋር ተወያዩ፡፡
-የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት 435 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለመምህራን በዕጣ እንዲተላለፉ መደረጉን አስታወቁ።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












