፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡
አዲስ አበባ | መጋቢት 02፣ 2016| NBC ETHIOPIA – አልቃይዳ በአረቢያ ፔንዙላ አካባቢ የቡድኑ መሪ ካሊድ ባታሪፍ መሞቱን አስታውቋል ፡፡ የቡደኑ የኢንተለጀንስ አገልግሎት እንዳስታወቀው ባታሪፍ መሞቱን እንጂ በምን ምክንያት እንደሞተ አልተገለጸም ተብሏል፡፡
የባታሪፍ ሞትን ተከትሎ ሳድ ቢን አቴፍ አል አውላኪ አዲሱ የቡድኑ መሪ እንደሆነ አልቃይዳ አስታውቋል ፡፡ አልቃይዳ ባታሪፍ አርበኛ እንደሆነና ጠንካራ ጂሃዲስት እንደነበር ገልጿል፡፡
ቡድኑ ለ15 ደቂቃ በለቀቀው ቪዲዮ የባታሪፍ አስከሬን በነጭና በጥቁር ከፈን ተሸፍኖ ወደ መቃብር ሲገባ ያሳያል፡፡ የሳውዲ ተወላጅ የሆነው ባታሪፍ በ2020 የአልቃይዳ መሪ ሆኖ የተሾመውሜሪካ መንግስት በተገደለው ቃሲም አል ሪሚ ቦታ ነበር፡፡
በባታሪፍ ቦታ አሁን የተሾመውን አል አውላኪ አሜሪካ በጥብቅ የምትፈልገው እንደሆነና ያለበትን ለጠቆመ 6 ሚሊዮን ዶላር እንደምትሰጥ ያስነበበው አልጀዚራ ነው ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












