ጾም ከሞላ ጎደል “ሙሉ ወይም ከፊል ከመብላት ወይም ከመጠጣት መታቀብ” ተብሎ ይተረጎማል። ወቅቱ እና ምክንያቱ ይለያይ እንጂ የኦርቶዶክስ፣ የእስልምና፣ የካቶሊክ፣ የአይሁድ፣ የሂንዱ እና የሌሎች እምነት ተከታዮች ሕግና ሥርዓት ባለው መንገድ ይፆማሉ።
የፆምን ሃይማኖታዊ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ በተለያየ ወቅት የወጡ ሳይንሳዊ የጥናት ውጤቶች ብናይ ፆም ለነፍስና ለመንፈሳዊ እርካታ ብቻ ሳይሆን፣ ለዓለማዊ ኑሯችን ለሥጋችንም ጭምር እንደሚጠቅም ይጠቁማሉ።
በእነዚህ ሳይንሳዊ ጥናቶች መሰረት አንድ ሰው ሲርበው ምን ዓይነት ስሜት እንደሚሰማውና ምን ዓይነት የጠባይ ለውጥ እንደሚያመጣ የሚገልፁ ሲሆን ÷ ውስጣዊ የሰውነት ለውጦችን እንዲሁም ውጫዊ ልዩነቶችን በማጥናት ምን ጥቅም እንደሚያስገኝ ለማሳየት ሞክረዋል።
በሆላንድ በተደረ ጥናት ቢያንስ ለስድስት ወራት እያቆራረጡ የሚፆሙ ሰዎች ስሜታቸው ጥሩ እንደሚሆን ተረጋግጧል። እነዚህ ጥናቶች በሙሉ እንደሚጠቁሙት ፆም ሰዎች ድብርት እንዳይሰማቸው፣ እንዳይናደዱ፣ ውጥረት እንዳይሰማቸው፣ ግራ መጋባት እንዳያጋጥማቸው ከማድረጉ ባሻገር፣ አእምሮ ውስጥ “ዶፓሚን” የተሠኘው ንጥረ ነገር እንዲመነጭ በማድረግ በተለይ ዕድሜያቸው በገፋ ሰዎች ላይ የደስታ ስሜት እንዲመጣ ይያደርጋል ይላሉ።
በተወሰነ ጊዜ የሚደረግ ጾም ክብደትን ለመቀነስ ፣ የልብና የደም ዝውውር ጤናን ለማሻሻል፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ለማስተካከል ፣የስኳር በሽታ እና የደም ዝውውር አደጋን ለመቀነስ አይነተኛ ሚና ይጫወታል።

የፆም ሳይንሳዊ የጤና ጥቅሞች
1.የሰውነት ምጣኔን እና አካል ብቃትን ያሻሽላል (Improves Body
Composition and Fitness)
2.የላቀ ደስታን ያጎናጽፋል (Promotes Greater Satiety)
3.የሰዉነታችንን ዉስጣዊ ግንባታ ከፍ ያደርጋል (Boosts Your Metabolism)
4.የሰዉነትን የስብ መጠን ይቀንሳል (Supports Fat Loss and Ketosis )
5.ኢንሱሊን የሚባለዉን የሰዉነት ቅመም ስራ ያግዛል (Encourages Better Insulin Sensitivity )
6.የልብና የደም ቧንቧ ጤንነት ላይ አወንታዊ ተጽኖ ያሳድራል (Improves Cardiovascular Health )
7.የደም ግፊት ይቀንሳል (Lowers Blood Pressure )
8.የደም ስኳርን ይቀንሳል (Decreases Blood Sugar )
9.እርጅናን ይከላከላል እድሜን ያረዝማል ( Slow Aging and Enhance Longevity )
10.በሰዉነት ዉስጥ ያሉ መርዛማ ንጥረ ነገሮች እንዲቀንሱ ይረዳል (decrease oxidative stress caused by free radicals)
11.በሰዉነት ዉስጥ ያሉ መርዛማ ንጥረ ነገሮች ጫናን ይከላከላል (Increases Resistance to Oxidative Stress)
12.አላስፈላጊ የሰዉነት ህዋሳትን ያስወግዳል (promotes the destruction of malfunctioning cells and tissues)
13.የአዕምሮ ጤናን ይጠብቃል (Protects Your Brain )
14.ጭንቀትን ይቀንሳል
15.ለሰዉነታችን ከጉዳት ማገገምን ያፋጥናል (Enhances Recovery From Injury )
16.ለሰዉነት ቆዳ ጤንነት ይጠቅማል (Supports Healthier Collagen in Skin )
17. ካንሰርን ይከላከላል
18. የነርቭ በሽታን ይቀንሳል ።
19. የእንቅልፍ መዛባትን ያስተካክላል ።












