አዲስ አበባ | የካቲት 12፣ 2016| NBC ETHIOPIA – የፓሪሴን ዠርመን አጥቂ ክልያን ምባፔ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ሪያል ማድሪድን ለመቀላቀል ተስማምቷል።

በመዲናው ክለብ ለአምስት ዓመት የሚያቆየው ዉል እንደሚፈርምና አመታዊ 15 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚከፈለው ተሰምቷል።
ከደሞዙ በተጨማሪ ለፊርማ 150 ሚሊዮን ዩሮ የቦነስ ክፍያ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ተከፋፍሎ እንደሚከፈለው መረጃው አክሏል።
በቀጣይ ክረምት ከሎስብላንኮች ጋር የሚለያየውን የሉካ ሞድሪች 10 ቁጥር ማሊያ እንደሚረከብም እንዲሁ። 25 ዓመቱ አጥቂ በ244 ጎሎች የፒ ኤስ ጂ የምንጊዜም ከፍተኛ አስቆጣር ነው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












