አዲስ አበባ | ጥር 28፣ 2016| NBC ETHIOPIA -ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ባለፈው የካቲት ስድስት 2023 ደቡባዊ ቱርክ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ እና ጉዳት የደረሰባቸውን የሀገሪቱን ዜጎች ለማጽናናት እንዲሁም ለመርዳት ቃል መግባታቸውን አስታውቀዋል ፡፡

ከቁስላቸውም እንዲያገግሙ አስፈላጊውን ዕገዛ እንደሚያደርጉም አደጋው የደረሰበትን አንደኛ ዓመት በሚያከብሩበት ወቅት ተናግረዋል ፡፡
በካራማናራ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ብዙ ሰዎች መሞታቸውን በዚህም ልባችን እንደተሰበረና በአዲስ መንፈስ እንደገና ማገገም አለብን ሲሉ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን በኤክስ ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
በቱርክ መሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ 53 ሺህ 537 ሰዎች ሲሞቱ፤ 107 ሺህ የሚሆኑ ደግሞ መቁሰላቸው ይታወሳል ፡፡፡፡ ዘገባው የቲአርቲ ወርልድ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












