-አዲስ አበባ | ጥር 29፣ 2016| NBC ETHIOPIA -ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በፖላንድ ቶሩን የቤት ውስጥ ሩጫ ውድድር በተለያዩ ርቀቶች ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፈዋል።
-በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 4ኛ በመውጣጥ ሲያሸንፎ በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር ሳሙኤል ተፈራ አንደኛ ወጥቷል፡፡
-በወንዶች 3 ሺህ ሜትር ሰለሞን ባረጋ 5ኛውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ÷ ጌትነት ዋለ እና ግርማ አዲሱ ደግሞ በቅደም ተከትል 2ኛ እና 4ኛ ወጥተዋል።
-በሴቶች የ800 ሜትር ሩጫ ደግሞ አትሌት ሀብታም ዓለሙ 1:57.86 የሆነ ፈጣን ሰዓት አስመዝግባ ውድድሩን አሸንፋለች።
-በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ በዛሬው ዕለት ጨዋታ አዘጋጇ ኮትዲቯር ከዴሞክራቲክ ኮንጎ እንዲሁም ናይጄሪያ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ይጫወታሉ፡፡
-የአንጎላ ብሔራዊ ቡድን የናይጄሪያ አቻውን ማሸነፍ ባይችልም የሀገሪቱ ባንክ ለብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች ቃለ የገባላቸውን የማበረታቻ ሽልማት ማበርከቱ ተገልጿል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












