አዲስ አበባ | ጥር 28፣ 2016| NBC ETHIOPIA -6ተኛው የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 14 መደበኛ ስብሰባ በዲፕሎማሲና በውጭ ግንኘነት ዙሪያ ለተነሱ ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከወር በፊት የባህር በር ፍላጎቷን ለማሳካት የቀይ ባህር በር ስምምነትን ከሶማሊላንድ ጋር ማድረጓን ተከትሎ የሚሰሙ ጩኸቶች ትክክል አይደለም የኢትዮጵያን ጥቅም ያላገናዘበ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ግንኙነቷን ከምዕራብ፣ከምስራቁም አጠናክራ እየሰራች ነው፤ በተለይ ከጎረቤት አገሮች ጋር ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዳላት እና እንደምትሰራ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው አንስተዋል፡፡
የዲፕሎማሲ ግንኙነታችን ብሄራዊ ጥቅምን ያስቀደመ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሪክስ የምንገባው ፣ኢጋድም የምገባው ለዚሁ ነው፤ የቀይ ባህር ስምምነት 120 ሚሊዮን ላላት ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማሳካት ነው ብለዋል፡፡
ይህም ማንም የሚጎዳ አይደለም ከሶማሊያ ጋር ያለንን ግንኙነት የሚጎዳ አይደለም ከየትኛው ህዝብ በተሻለ የሶማሊያ ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የተቃረበ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ የሶማሊያን ህልውና ለማስጠበቅ በታሪክ በርካታ ስራዎች አከናውናለቸ አሁንም ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በቀይ ባህር ዙሪያ የሚነሱ ጉዳዮችን ለማስተካከል ብዙ ጩኸት አለ የዓለም ህዝብ እንደሚዳኘን እንጠብቃለን ፤ የምንፈልገው ልማት እንጂ ግርግርና ውጊያ አንፈልግም ፤
ኢትዮጵያ ወረራ አከናውና አታውቅም ወራሪ ከመጣ ግን ለመመከት ችግር የለብንም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












