አዲስ አበባ | ጥር 28፣ 2016| NBC ETHIOPIA -ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ዛሬ እየተደረገ ባለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለተነሳላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ ባሉበት ወቅት ነው።
የቆዩ ስብራቶች ኢኮኖሚዉን በማደግና በመፈተን ዉስጥ እንዲወድቅ ቢያደርጉትም ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ እድገት የሚታይ ነዉ ሲሉ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በገቢና ወጪ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ዘንድሮ በ6ወር ወስጥ 270 ቢሊየን ብር ታቆዶ 265 ቢሊየን ብር ገቢ ሆኗል በዚህም 98 በመቶ የሚሆነዉን ማሳካት ተችሏል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በኢኮኖሚው ዙሪያ ምላሽ እየሰጡ ይገኛል፡፡
ድርቅን ተከትሎ የሚመጣን ፈተና ለመመከት በ2016 በጀት ዓመት ሶስት ሚሊየን ሄክታር መሬት መታረሱንና ከዚህም ከ120 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ መክፈል አቅቷታል የተባለው 33 ሚሊየን ዶላር የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሁለት ቀን ገቢ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በምላሻቸው ለግል ሴክተሩ ከ170 ቢሊየን ብር በላይ ብድር መሰጠቱን ጠቁመው ባንኮችን ከመውደቅ መታደግ መቻሉንም አንስተዋል፡፡
ከዚህ ባሻገር በግብርናው ዘርፍ እንደሚታወቀው ከፍተኛ የሆነ እመርታ እየመጣ እንደሆነ ገልፀው አሁን ከሰራነው በላይ መስራት ብንችል ብዙ ቀዳዳዎችን መድፈን እንችላለን ሲሉ ተናግረዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












