አዲስ አበባ | ጥር 28፣ 2016| NBC ETHIOPIA -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች በተደረገው ውይይት ከህዝቡ ሶስት ዋና ዋና ጥያቄዎች መነሳታቸውን ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ክልሉን በተመለከተ በሰጡት ምላሽ የልማት፣ የህገ መንግስት ማሻሻልና የወሰን ጥያቄዎች በተደረገው ውይይት ከህዝቡ የተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
መንግስት በአማራ ክልል የሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ብዙ ርቀት ሄዷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአብነትም 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር አውጥተን በአባይ ወንዝ ላይ በአይነቱ ልዩ የሆነ ድልድይ ተገንብቷል ብለዋል።
በጎርጎራ ፕሮጀክት አማካኝነት የክልሉን ቱሪዝም የሚያነቃቃ ስራ እንየተከናወነ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
በአገራዊ የምክክር ኮሚሽን በኩል ሌሎች ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ይሰራልም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ።
በአማራ ክልል የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በ5 ዓመታት 3 ሺ 200 ኪ.ሜ የመንገድ ዝርጋታ መጀመሩንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) ገልጸዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












