አዲስ አበባ | ህዳር 06 2016| NBC ETHIOPIA -በኢትዮጵያ በሰአት 3 ህፃናት በቀን 65 ህፃናት በአመት ዉስጥ ደግሞ 23,485 ህፃናት በሳንባ ምች በሽታ ምክንያት ህይወታቸው ያልፋል።

የሳንባ ምች በሽታን በመከላከል እና በማከም የሕፃናትን ህይወት እንታደግ! በሚል መሪ ቃል በሃገራችን ለ4ኛ ጊዜ በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ የአለም የሳንባ ምች ቀን ተከበሮ ውሏል።
የሳንባ ምች በሽታ በደም ውስጥ የሚገኝ የኦክስጅን መጠን እንዲያሽቆለቁል ከማድረጉ ባሻገር ሕሙማን በከፍተኛ የትንፋሽ እጥረት እንዲሰቃዩም ያደርጋል።
መንስኤው በቤት ዉስጥ ያለ የአየር መበከል ፣ ንፅህናን ያለ መጠበቅ እና የተመጣጠነ ምግብ አለመዉሰድ በተለይ ደግሞ ህፃናት በቂ የእናት ጡት ወተት አለማግኘት እና የመሣሠሉት ናቸው። እራሳችንን ከነዚህ ጉድለቶች መጠበቅ ከቻልን መከላከል እንደሚቻል በዉይይቱ ተነስቷል።
የሕክምና ኦክስጅን አቅርቦት መኖር ወይም አለመኖር የእነዚህን ሕሙማን ሕይወት የማትረፍ ወይም ያለማትረፍ ጉዳይ እንደሚሆን በውይይቱ ተገልጿል።
የማህበረሰብ ንቅናቄ በመፍጠርና ማህበረሰቡ ስለ ሳምባ ምች ያለዉን ግንዛቤ በመጨመር በቤት ዉስጥ የሚያደርጉት እንክብካቤ አስተማማኝ እንዲሆን ማስቻል እንደሚገባ በመድረኩ የተገለፀ ሲሆን በቂ ግንዛቤ የሌላቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ እንደሚሰራም ተገልፀዋል።
በአስናቀች መላኩ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












