አዲስ አበባ | ህዳር 7፤ 2016| NBC ETHIOPIA -ኢትዮቴሌኮም ከትራንስፖርት እና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር፣ ከነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን፣ ከመንገድ ደህንነትና ፈንድ አገልግሎት ጋር እና ከኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ጋር በመተባበር የትራንስፖርት ሴክተሩንና የነዳጅ አቅርቦት ትስስር አስተዳደሩን የሚያዘምኑ አዳዲስ የዲጅታል ሶሉሽን አገልግሎቶችን የሚያስተዋዉቅበትንና በይፋ የሚያስጀምርበትን መርሐግብር በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ኩባንያዉ በዛሬዉ ዕለት የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለትን ባማከለ የዲጂታል ሥርዓትን ለማከናወን የሚያስችል የነዳጅ አቅርቦት ትስስር አስተዳደር ሶሉሽን (Fuel Supply Chain Management System) በማበልፀግ ተግባራዊ አድርጓል። ይህም ግልጽነት ያለዉ የነዳጅ አቅርቦትና ግብዕይ ለማስፈን ይረዳል ተብሏል።
በሌላ በኩል ኩባንያዉ የማንዋል የነዳጅ ኩፖን ሽያጭ አገልግሎት አሰራርን ወደ ወረቀት-አልባ የዲጅታል ኩፖን በመቀየር አዲስ አሰራር ያስተዋወቀ ሲሆን የነዳጅ ማደያዎችን የአገልግሎት አማራጭ ለማሳደግ ይረዳል።
በተመሳሳይ ሁኔታ የሶስተኛ ወገን የመድን አገልግሎት በዲጂታል ስርዐት አማካኝነት ለመስጠት የሚያስችል ሶሉሽን ከትራንስፖርት እና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር እና ከመንገድ ደህንነት እና ፈንድ ጋር በመተባበር ይፋ አድርጓል።
ዲጅታል ኢትዮጵያን እዉን በማድረግ ሂደት ዉስጥ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ የሚገኘዉ ኢትዮቴሌኮም ማደያዎች በዲጅታል መንገድ እንዲገበያዩ ባደረገዉ መሠረት ከ 1.4 ትሪሊየን ብር በላይ በቴሌብር ግብይት መፈፀሙን ገልጿል።
ሊያ ክብሮም
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












