አዲስ አበባ | ህዳር 7፤ 2016| NBC ETHIOPIA -የአዲስ አበባ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ በ2016 ከ33 ሺህ በላይ አዲስ ሰልጣኞችን ከሰኞ ህዳር 10/2016 ጀምሮ ምዝገባ እንደሚጀምር አስታውቋል::

ቢሮው የዘንድሮ የሰልጣኞች ቅበላን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በ22 ዘርፎችና በ123 የስልጠና አይነቶች ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል::
ምዝገባው ከደረጃ 1 እስከ 5 ለተከታታይ አስር ቀናት በ www.aatvetb.edu.et ድረ ገፅ በመግባት መመዝገብ እንደሚቻል ተመላክቷል::
አክረም ኑርያ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












