አዲስ አበባ | ህዳር 07 2016| NBC ETHIOPIA -ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በግማሽ አመት የስራ አፈፃፀም የመጣበትን ሁለት አላማዎች ማለትም በቴሌኮም እና በፋይናንስ ዘርፍ በመሰማራት በርካታ ደንበኞችን እያፈራ እንደሚገኝ በአዲሱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሄልፑትን በኩል ግልጿል፡፡

በአሁኑ ሰአት በጠቅላላው ወደ 4 ሚሊዮን የሚሆኑ ደንበኞችም አሉት በፋይናንስ ዘርፉ እንዲሁ ከብሔራዊ ባንክ በባለፈው ነሀሴ ፍቃድ በማግኘት ኤምፔሳ በተሰኘው አገልግሎቱ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ደንበኞች ማፍራቱንና ወደ 12 ከሚሆኑ ባንኮች ጋር አብሮ እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
2 ሺ በላይ የቴሌኮም ማማዎች ማቀም እንደቻሉ ፤ በየወሩም 150 ማማዎች እየተገነቡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡በቀጣይም ይህንን በማስፋት ጥራት ያለው እና ፈጣን የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎትን ለማስፋፋት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
በ የአብስራ ሚሊዩን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












