አዲስ አበባ | ጥቅምት 22 2016| NBC ETHIOPIA – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል::

በአማራ ክልል ተከስቶ የነበረዉ አለመረጋጋት ወደ ሰለማዊ እንቅስቃሴ እየተመለሰ መሆኑን ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በመግለጫቸው አስታውቀዋል።
የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ክልሉን ወደ ሰላም ለመመለስ የተቋቋመዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ እዝ ያከናወናቸዉን ተግባራት መገምገሙንና በክልሉ የተፈጠረዉን አለመረጋጋት ለመፍታት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሕግ የማስከበር ሥራ መሥራቱን የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር) ገልጸዋል ።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ እዝ በክልሉ በተፈጠረዉ አለመረጋጋት ወደ 3 ሺህ 200 የሚጠጉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ነው የገለፁት ። በህግ ቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል1 ሺህ 51 የሚሆኑት ተሃድሶ ተሰጥቷቸዉ ወደ ማህብረሰቡ እንዲቀላቀሉ መደረጉም ሚኒስትሩ አብራርተዋል ።
በሰላማዊት ወልደገሪማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
See insights and ads
All reactions:
99












