አዲስ አበባ | ጥቅምት 22፤ 2016| NBC ETHIOPIA – 25ኛው የጤና ዘርፍ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ሲሆን የጤና ሚኒስቴር በየዓመቱ በጤናው ዘርፍ የተሰሩ ስራዎችን የሚገመገምበትና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን ለሚመለከታቸው አካላት አቅርቦ ውይይት የሚደረግበት ዓመታዊ ጉባኤ ነው።

የዘንድሮው ጉባኤም “ጠንካራ የጤና ፋይናንስ ለዘላቂ የጤና ልማት” በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 21-23 በመካሄድ ላይ ይገኛል። በጉባኤው ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያከናወናቸው ስራዎችና በቀጣይ ያቀዳቸው ተግባራት ቀርበዋል።
የጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) የጤና ዘርፉን በማዘመን ረገድ መስሪያ ቤታቸው የአየር አምቡላንስ ለመግዛት በሂደት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በትላንትናው ዕለት በተመረጡ የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የመስክ ምልከታ የተደረገ ሲሆን ዛሬና ነገ በሚኖረው ቆይታ የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ይቀርባል። ሚኒስቴሩ ያስቀመጣቸው ቀጣይ እቅዶች ላይም ውይይት የሚደረግ ይሆናል።
በተጨማሪም የሶስት አመታት የጤናው ዘርፍ እድገት እና ኢንቨስትመንት እቅድ በመድረኩ እንደሚቀርብ ይጠበቃል።

የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የጤናው ዘርፍ ባለሙያዎች የእውቅና መርሀ ግብር የሚካሄድ ሲሆን የቀጣይ ዓመት የጉባኤው አዘጋጅ ክልል ይፋ ይደረጋል።
በጉባኤው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ ከመዲናዋና ከተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች የተውጣጡ የዘርፉ ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነውበታል።
በመቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv












