አዲስ አበባ | ጥቅምት 22 2016| NBC ETHIOPIA – ባንኩ ከአስር አመት በፊት ያስጀመረውን የሲቢኢ ኑር ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ምክንያት በማድረግ ከዛሬ ጥቅምት 22 /2016 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ወር በሚቆዩ የተለያዩ መርህ ግብሮች ለማክበር የመክፈቻ መርሀግብር አካሂዷል።

በማስጀመርያ መርሃግብሩ ላይ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ ባደረጉት ንግግር፥ ሲቢኢ ኑር ለረጅም ጊዜ በወለድ ምክንያት ከባንክ ርቀው የነበሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን በተለይ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ከወለድ ነጻ አገልግሎት ማቅረብ የቻለ ሆንዋል ብለዋል።
በ23 ቅርንጫፎች የተጀመረው የሲቢኢ ኑር ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ዛሬ ሰፍቶና አድጎ በባንኩ 153 ቅርንጫፎች እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉም ሲሆን፣ ባንኩ በሲቢኢ ኑር የ አስር አመት ቆይታ ላስመዘገባቸው አበረታች ውጤቶች ባለ ድርሻ አካላትን አመስግነዋል።
የሲቢኢ ኑር ምክትል ፕሬዝዳንት ኑሪ ሁሴን በበኩላቸው፣ በ10 ሺ ደንበኞች የተጀመረው አገልግሎቱ አሁን ላይ 6.4 ሚሊየን ደንበኞችን ማፍራት መቻሉን ገልጸው፥ በቀጣይ የሸርያ ህጉን በጠበቀ መልኩ አሰራርን በማዘመን የላቀ ስኬት ለማስመዝገብ እንደሚሰራም ተናግረዋል።
ባንኩ ከ 2006ዓ.ም ጅማሮ አንስቶ አሁን እንከደረሰበት በሲቢኢ ኑር የደረሰበትን ስኬትና የአሰራራር ሁኔታ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ም/ፕሬዚዳንት ሼህ አብዱል ከሪም ሼህ በድረዲን በመርሀግብሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በማስጀመሪያ መርሃግብሩ ላይ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ፣ የሲቢኢ ኑር ምክትል ፕሬዝዳንት ኑሪ ሁሴን፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ም/ፕሬዚዳንትን ጨምሮ የብሔራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የስራ ኃላፊዎች፣ የሸርያ አማካሪ ኮሚቴ አባላት እና ደርበኞች ተገኝተዋል።
በሰላማዊት ወንድወሰን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












