አዲስ አበባ | ጥቅምት 21፤ 2016| NBC ETHIOPIA -እስራኤል በጃባሊያ የስደተኞች ካምፕ ባደረሰችው ጥቃት የሀማስን አዛዥ መግደሏን ይፋ አድርጋለች፡፡

በጥቃቱ 50 ስደተኞች እና አደጋ የደረሰባቸውን ለመታደግ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች ጭምር ሕይወታቸውን ሲያጡ 1 መቶ 50 የሚሆኑ ዜጎች ደግሞ ቆስለዋል ።
የሀማስ ቃል አቀባይ ሀዘም ቃሴም በበኩላቸው ከፍተኛ የተባለ አዛዥ በካሞፑ ውስጥ አልነበረም ሲሉ አስተባብለዋል። ቃሴም ይህ እስራኤል ንጹሃንን ለማጥቃት ስትፈልግ እንደሰበብ የምትጠቀምበት ነው ብለዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram –https://t.me/nbcethiopiatv