አዲስ አበባ | ጥቅምት 22፤ 2016| NBC ETHIOPIA -የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል::

በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም የከተማ አስተዳደሩ መዋቅር አካላት ተናብበው እና ተቀናጅተው የሰሯቸው ስራዎች ውጤታማ ሆነው ተጠናቀዋል ብለዋል፡፡
ለህዝብ የገባነውን ቃል ተግባራዊ ለማድረግ የሰራናቸው ስራዎች የነዋሪውን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እና ማህበራዊ ፍትህ ማንገስ ጀምረዋል ያሉት ከንቲባ አዳነች በግምገማችን ጥንካሬዎቻችንን በማላቅ ድክመቶቻችንን እና መንስኤዎቻቸውን ለይተን በማረም ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት ማገልገላችንን እንቀጥላለን ብለዋል::
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram –https://t.me/nbcethiopiatv












