አዲስ አበባ | ጥቅምት 08 2016| NBC ETHIOPIA -ብራዚላዊው የአል- ሂላል አጥቂ ትላንትና በአለም ዋንጫ ማጣሪያ በኡራጋይ ሁለት ለምንም በተሸነፉበት ጨዋታ፣ የጉልበት ጅማት መበጠስ (ACL) ጉዳት አጋጥሞት በሳንስ ከሜዳ መውጣቱ ይታወሳል።
የ31 አመቱ ተጨዋች ለምን ያህል ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ባይገለጽም፣ ከጉልበት ጅማት መበጠስ ጉዳት ለማገገም ከ8 እስከ 10 ወራት ይፈጃል።
የብራዚል የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪው፣ ካለፉት ሁለት የውድድር አመታት ወዲህ በተደጋጋሚ ጉዳት እየተፈተነ ይገኛል።
ኔይማር” እጅግ አስከፊና መጥፎ ጊዜ “ ሲል በኢንስታግራም ገጹ ላይ አስፍሯል።
አክሎም፣ “ጠንካራ እንደሆንኩ አውቃለሁ፣ ነገር ግን ይህ ወቅት ከየትኛውም ጊዜ በላይ የጓደኞቼና ቤተሰቦቼን ድጋፍ የምሻበት ነው” ብሏል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
See insights and ads
All reactions:
11












