አዲስ አበባ | ጥቅምት 07 2016| NBC ETHIOPIA -የብራዚል ብሄራዊ ቡድን አምበል ኔይማር ዡኒየር የግራ ጉልበቱ ላይ ጉዳት አስተናግዷል፡፡

ተጨዋቹ ጉዳት ያስተናገደው በ2026 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ብራዚል በዩራጋይ 2 ለ 0 በተሸነፈችበት ግጥሚያ ላይ ሲሆን በጨዋታው ከ44 ደቂቃዎች በላይ መጫወት አልቻለም፡፡
የ31 ዓመቱ ኔይማር ከጉዳቱ በኋላ የሰውነት ሚዛኑን ተቋቁሞ መራመድ ባለመቻሉ በምርኩዝ ከሜዳ ለመውጣት ተገዷል፡፡
ተጨዋቹ በጉዳቱ ሳቢያ ለምን ያህል ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ ግን በውል አልተገለጸም፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












