አዲስ አበባ | ጥቅምት 07 2016| NBC ETHIOPIA – ላለፉት 6 ወራት ተቋርጦ የነበረው የስደተኞች የምግብ አቅርቦት ዳግም በመጠለያ ጣቢያዎች መድረስ መጀመሩን የኢፌዴሪ የስደተኞችና ተመላሽ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጠይባ ሀሰን ገልፀዋል።

የምግብ አቅርቦት መቋረጡም በስደተኞች ላይ የሞት ጉዳትን ጨምሮ ጉዳት ማድረሱ አንስተው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ ግን ሰብዓዊ ድጋፎች ማቅረቡን ገልፀዋል።
በጄኔቫ በተባበሩት መንግስታት በተዘጋጀው የስደተኞች ኮሚሽነር 74ተኛ የስራ አስፈፃሚዎች ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ የስደተኞችና ተመላሽ አገልግሎት በጉዳዩ ላይ የሚታዩ ችግሮች ለመቅረፍ በርካታ ጉዳዮች ላይ መሞከራቸው አንስተዋል።
የስደተኞች ቀጣይ እጣፈንታ ለመወሰን እና የተለያዩ የልማት ስራዎቸ ላይ ለመምከር ታህሳስ ላይ ጉባኤ እንደሚካሄድ ተነስቷል።
ኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ስደተኝነት ጠያቂዎች በ26 መጠለያዎች ይገኙበታል ተብሏል።
በሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












