አዲስ አበባ | መስከረም 25 2016| NBC ETHIOPIA – የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ በሚቀጥለው ሳምንት የሶላር መብረቅ ሊከሰት ይችላል ሲል አስጠንቅቋል::

የተቋሙ ማስጠንቀቂያም በሚቀጥለው ሳምንት በተለይም በፈረንጆቹ ጥቅምት 10 እና 11 ባሉት ቀናት ውስጥ ከባድ የፀሀይ መብረቅ ወይም ሞገድ ሊከሰት ይችላል ብሏል።
ይህን የናሳን ማስጠንቀቂያ መሰረት በማድረግ በመላው ዓለም ኢንተርኔት ሊቋረጥ ይችላል የሚሉ ዜናዎች በዓለም ላይ በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ።

ይህ ዜና በስፋት መሰራጨቱ ያሳሰበው ናሳም ኢንተርኔት በመላው ዓለም ይቋረጣል በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን አስታውቋል።
ድርጅቱ አክሎም በሚቀጥለው ሳምንት በፀሀይ ሀይል ምክንያት ይፈጠራል በተባለው መብረቅ የኢንተርኔት አገልግሎት ሊቋረጥ የሚችልበት ምንም አይነት ግልጽ ስጋት የለም ማለቱን አልአይን አማርኛ ዘግቧል፡፡
YouTube https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram -https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












