አዲስ አበባ | መስከረም 24 2016| NBC ETHIOPIA — የመደመር እሳቤ በኢትዮጵያ አሳታፊ የፖለቲካ ስርዓት እውን እንዲሆን ያደረገ የፍትሃዊነት መንገድ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ።

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የክልሉና የፌደራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ታድመዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳደር አሻድሊ ሀሰን በዚሁ ጊዜ፤ ኢትዮጵያዊያን በረዥም ጊዜ የአብሮነት ታሪካቸው በተደመረ አቅም ነጻነቷ የተጠበቀ አገር ለትውልዱ ማስረከብ መቻላቸውን ተናግረዋል።
አገራዊ ለውጡን ተከትሎም ኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀቶችን መሰረት ባደረገው የመደመር እሳቤ እየተመራች በርካታ ድሎችን አስመዝግባለች ነው ያሉት።
በተጨማሪም የመደመር እሳቤ በሌሎች የፓለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እንዲሁም ዲፕሎማሲያዊ መስኮች በርካታ ድሎች እንዲመዘገቡ አድርጓል ነው ያሉት።
የመደመር እሳቤ በኢትዮጵያ ውስጥ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር የአገር ህልውናን የማጽናት መንገድ እንደሆነ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












