አዲስ አበባ | መስከረም 25 2016| NBC ETHIOPIA – በዛሬው ዕለት ታሪክ ሲወሳ ፣ እንደ እ.ኤ.አ ጥቅምት 6 ፣ 1981 – የግብፁ ፕሬዝዳንት አንዋር ሳዳት ወታደራዊ ሰልፍን እየተመለከቱ በነበሩበት ወቅት ካይሮ በሚገኙ አክራሪ የእስልምና እምነት ተከታይ ቡድኖች ተገደሉ።

አንዋር ሳዳት ከመገደላቸው በፊት እ.ኤ.አ በ 1978 የሰላም የኖቤል ሽልማትን ከእስራኤሉ ሜናኬም ቤጊን ጋር ወስደው ነበር። ፕሬዝዳንቱ ከእስራኤል ጋር ሰላም ለማውረድ በአሜሪካ አሸማጋያነት የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው በሌሎች የአረብ መሪዎች እንዲወገዙ አድርጓቸው ነበር፡፡

እንደ ኢኤአ ጥቅምት 15 1970 – ጥቅምት 6 1981 ድረስ ሶስተኛው የግብፅ ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገሉት አንዋር ሳዳት ከምዕራባውያን ጋር የመግባባት ዲፕሎማሲን ለማምጣት ጥረት ያደረጉ መሪ እንደነበሩ ታሪካቸው ይገልጻል፡፡
YouTube https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram -https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












