አዲስ አበባ | መስከረም 24 2016| NBC ETHIOPIA – የ2030 የዓለም ዋንጫ በሶስት አህጉራት ውስጥ በሚገኙ ስድስት ሀገራት እንደሚካሄድ ፊፋ ገልጿል፡፡

የዓለም ዋንጫው ለመጀመሪያ ጊዜ በሶስት አህጉሮች ማለትም በአፍሪካ፣ በአውሮፓ እና በደቡብ አሜሪካ ውስጥ በሚገኙ ስድስት ሀገራት ይካሄዳል ተብሏል።
በዚህም መሰረት የአለም ዋንጫው 100 አመት በሚሞላበት የ2030 ዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታዎች አርጀንቲና ፣ ዩራጋይ እና ፓራጓይ ውስጥ እንደሚደረግ ቢቢሲ ዘግቧል።
ከመክፈቻ ጨዋታዎች በመቀጠል የሚደረጉ ሁሉም የውድድሩ ቀሪ ጨዋታዎች የውድድሩ ዋና አዘጋጅ በሆኑት በአፍሪካዊቷ ሞሮኮ፣ ስፔን እና ፖርቹጋል ውስጥ እንደሚደረጉ ታውቋል።
የአለም ዋንጫ ውድድር በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በሶስት አህጉር የሚደረግ ሲሆን ስድስቱም አዘጋጅ ሀገራት በቀጥታ ያለማጣሪያ ለውድድሩ እንደሚያልፉ ተጠቁሟል።
ይሁን እንጂ የዓለም ዋንጫ በሶስት አህጉራት ውስጥ በሚገኙ ስድስት ሀገራት የማዘጋጀት ሀሳቡ በቀጣይ ዓመት በሚካሄደው የፊፋ ጉባዔ ላይ መጽደቅ ይጠበቅበታል ተብሏል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












