አዲስ አበባ | መስከረም 11 2016| NBC ETHIOPIA – የሱዳኑ መሪ በሀገራቸው የተከሰተው ጦርነት ወደ ጎረቤት ሀገራት ሊስፋፋ ይችላል ሲሉ በተባባሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተናገሩ።

የሱዳን
ጦር መሪ ጀነራል አብድል ፋታህ አል-ቡርሃን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በጀነራል ሐምዳን ዳጋሎ የሚመራውን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ሽብርተኛ
ቡድን ብሎ እንዲፈርጀውም ጥያቄ አቅርበዋል።
በሌላ
በኩል የፈጥኖ ደራሹ ኃይል መሪ ጀነራል ሃምዳን ደጋሎ የተኩስ አቁም ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ሱዳን
ከባለፈው ሚያዚያ ጀምሮ በእርስ በርስ ጦርነት የነበርች ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩት ደግሞ ሀገሪቱን
ጥለው ተሰደዋል።
የተባበሩት
መንግሥታት ላይ ንግግር ያደረጉት ጀነራል አል ቡርሃን ፓርቲያቸው
የሰላም ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጠዋል።
“ጦርነቱን
ለማቆምና እና የሕዝባችንን ስቃይ ለመግታት ዝግጁ ነን” ነገር ግን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ፈቃደኛ አይደለም ብለዋል።
ተቀናቃኛቸው
ጀነራል ደጋሎ ለተመድ በላኩት ተንቀሳቃሽ ምስል ግጭቱን በንግግር ለመፍታት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ሁለቱ
የጦር ጀነራሎችን ልዩነቶቻቸውን በንግግር እንዲፈቱ አሜሪካ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ግብጽ ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።
የፈጥኖ
ደራሹ ኃይል አባላት በመላው ሱዳን መሰማራታቸውንና ጀነራል አል ቡርሃን እንደ ስጋት ማየታቸውን ተከትሎ ነው የሱዳን የእርስ በርስ
ጦርነት ባለፈው ሚያዚያ ወር ነበር የፈነዳው።
የመጀመሪያዋን
ጥይት ማነው የተኮሰው የሚለው አከራካሪ ቢሆንም ግጭቱ በፍጥነት ጨምሮ በመላ ሃገሪቱ ተስፋፍቷል።
በአውሮፓውያኑ
2021 የተፈፀመውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ ጀነራል አል ቡርሃን የሱዳን መሪ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ዓለም አቀፍ ዕውቅና
ለማግኘት በመላው ዓለም ሲዘዋወሩም ከርመዋል።
ለተባበሩት
መንግሥታት ባደረጉት ንግግራቸው ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ከሩሲያ ቫግነር ቡድን ጋር ያለውን ግንኙነትም አንስተዋል።
ቅጠረኛው
ቫግነር ቡድን በሱዳን ጨምሮ በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ሊቢያ፣ ሞዛምቢክ እና ማሊ እንደሚንቀሳቀስ ይታመናል።
“የጦርነቱ
አደጋ አሁን ለጎረቤት ሃገራትም እና ለመላው ዓለም ሰላምና ፀጥታ ስጋት እየሆነ ነው። አማፂያኑ ሕጋዊ ያልሆኑ እና ሽብርተኛ ከተባሉ
ሃገራትና ድርጅቶች ድጋፍ እያገኙ ነው” ብለዋል።
የቀድሞው
መልዕክተኛ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ወሲባዊ ጥቃት በመፈፀም፣ በዝርፍያ እና በግድያ የወቀሱ ሲሆን የሱዳን ጦር ኃይል ደግሞ ሰላማዊ
ዜጎች የሚኖሩበትን ሳይለይ የአየር ጥቃት ሰንዝሯል ብለዋል።
እንደ
ቢቢሲ ዘገባ የሄሜቲ ተዋጊዎች ብዙውን ጊዜ በርካታ ሰዎች በሚኖሩባቸው ከተሞች የሚሰፍሩ ሲሆን የሱዳን ጦር እነዚህ ሰፈሮች የጦርነት
ዒላማ ናቸው ብሎ ያምናል።
በሃና ተሰማ
YouTube
– https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok
– https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook
-https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram
-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA












