የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የገጠር መንደሮችንና ከተሞችን በፀሀይ ኃይል ማመንጫ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚስችል 25ቱ ከተሞች የሶላር ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክት ቀርፆ ወደ ስራ ገብቷል፡፡

የኦፍ ግሪድ ፕሮጀክቱ የገንዘብ ምንጭ የአፍሪካ ልማት ባንክና የኢትዮጵያ መንግስት፤ አጠቃላይ ወጪው 20 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እና 161 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ነው፡፡
እየተገናባ የሚገኘው የሶላር ፕሮጀክት ዋና ዓላማ ከዋናው ግሪድ ርቀው የሚገኙ 25 የገጠር ቀበሌዎችን በፀሀይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ሲደረግ የዕውቀት ሽግግርንና ሰፊ የስራ ዕድል የሚፍጥር ሲሆን፤ 145 ሺህ 169 አዳዲስ ደንበኞችም የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡
አጠቃላይ 8 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው ይህ ፕሮጀክት፤ 68 ነጥብ 7 የመካከለኛና 233 ነጥብ 3 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ ይከናወንበታል፡፡
በግንባታው በሁለት የቻይናና በአንድ የኮሪያ ኩባንያዎች እየተከናወነ ሲሆን የፕሮጀክት አጠቃላይ አፈጻፀም 30.37 በመቶ ደርሷል፡፡
ተቋሙ እ.ኤ.አ በ2030 ከዋናው ግሪድ 65 በመቶ እንዲሁም በአማራጭ የኃይል ምንጮች 35 በመቶ የሚሆነውን ህብረተሰብ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ርብርብ እያደረገ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ ያመለክታል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook
-https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram –https://t.me/nbcethiopiatv












