አዲስ አበባ | መስከረም 11 2016| NBC ETHIOPIA – በአልጄሪያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ከአልጄሪያ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዩሱፍ ሸረፋና ከኤር አልጄሪ ዳይሬክተር ያሲን ቤንስሌማኔ ጋር በጋራ በመሆን በኢትዮጵያና በአልጄሪያ መካከል የመጀመሪያ የሆነውን ቀጥታ የአውሮፕላን በረራ በዛሬው እለት አስጀምረዋል።

በማስጀመሪያ መርሃግብሩ የአልጄሪያ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዩሱፍ ሸረፋ የተመራ ልዑክቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ዳይሬክተር ጄነራል በአምባሳደር ፍስሃ ሻወል አቀባበል ተደርጐላቸዋል።
ሁለቱ አገራት የትራንስፖርትና የአቪዬሽን ዘርፉን ለማጠናከር ቀደም ሲል ከገቧቸው ስምምነቶች መካከል አንዱ መሆኑ ተገልጿል።
እንደ ኢፕድ ዘገባ ኢትዮጵያና አልጄሪያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የተጀመረው እ.አ.አ በ1960 ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ነው።
አልጄሪያ በአዲስ አበባ እ.አ.አ በ1976 እንዲሁም ኢትዮጵያ በአልጀርስ እ.አ.አ በ2016 ኤምባሲ በመክፈት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ሲያጠናክሩ ቆይተዋል።
YouTube– https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok– https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA












